1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኬንያ ፍትህና የሞት ቅጣት ፍርድ

ቅዳሜ፣ ጥር 27 2015

የኬንያ የሰብአዊ መብት ኮሚሽን የሞት ቅጣትን በሃገሪቱ ለመሻር እንቅስቃሴ ጀምሯል። ምንም እንኳን የሞት ቅጣት አሁንም በኬንያ ህጋዊ ቢሆንም ወንጀልን በመዋጋት ረገድ ውጤታማ አለመሆኑን እና ድሆች ላይ ብቻ ማነጣጠሩን የኬንያ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን አጽኖት ሰጥቷል። በኬንያ የመጨረሻው የሞት ቅጣት የተፈፀመዉ ከ 35 ዓመታት በፊት ነዉ።

https://p.dw.com/p/4N5X6
Kenia wartet mit Spannung auf das Urteil des Obersten Gerichtshofs zu den Wahlen | Gebäude
ምስል Tony Karumba/AFP

በኬንያ የጨረሻዉ የሞት ቅጣት ፍርድ የተፈፀመዉ ከ 35 ዓመታት በፊት ነዉ

የኬንያ የሞት ቅጣት ህግ በአብዛኛዉ ደኃዉ ማኅበረሰብ ላይ ማነጣጠሩ ተመልክቷል።  የሰዉ ልጅ ባልፈፀመዉ ወንጀል ለ18 ዓመታት በእስር ላይ መቆየት ማለት ምን ማለት እንደሆን መገመት እንብዛም ከባድ አይደለም። ኬንያዊዉ ጴጥሮስ ኦኮ የሞት ፍርድ የተበየነበት እውነታም ይህ ነዉ። በጎርጎረሳዉያኑ 2016 ዓ.ም የሃገሪቱ ፕሬዚደንት ለእስረኞች ምህረት ሲሰጤ፤ የሞት ፍርድ የተበየነባቸዉ ጴጥሮስ ኦኮ ከ 18 ዓመታት እስር በኋላ ይቅርታዉ ደርሶች እና እድለኛ ሆነዉ ከእስር ተለቀዋል። ጴጥሮስ ኦኮ በኬንያ ድሆች ላይ በተሳሳተ መንገድ የሞት ፍርድ መበየኑ የተለመደ ሆንዋል ይላሉ። 

« የፈረሰ የፍትህ ስርዓት ነበር ያለን። አንዳንድ ፍርድ ቤቶች በሚያነቡት ብይን በዳኞች የተጻፉ አልነበሩምም። ፍርዱ የሚመጣዉ ከሌላ ቦታ ተጽፎ ነበር። ለዚህም ነው በእስር ላይ የሚገኙት አብዛኞቹ ታሳሪዎች የማይገባቸውን ፍርድ ተበይኖባቸዉ ተዘግቶባቸዉ እና ታስረዉ የሚገኙት።»

በጎርጎረሳዉያኑ ጥር 2023 ዓ.ም በኬንያ የሚገኙ የሰብዓዊ መብት ቡድኖች ያቀረቡት ዘገባ እንደሚያሳየው የሞት ፍርድ ከተፈረደባቸው ሰዎች መካከል አብዛኞቹ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ናቸዉ። እነዚህ እስረኞች ትክክለኛ ዉክልና ወይም ጠበቃ ማግኘት አይችሉም። በጎርጎረሳዉያኑ አቆጣጠር በ80 ዎቹ እና በ90ዎቹ ዓመታት የታሰሩት ሰዎች የሀገሪቱ የፍትህ ስርዓት በሙስና ሲበላሽ በቁጥጥር ስር የዋሉ መሆናቸዉ ተገልጿል። ይሁንና የተፈረደባቸዉ ሁሉ ግን ጥፋተኞች እንዳልነበሩ ተነግሯል። ከነዚህ መካከል ጴጥሮስ ኦኮ ይገኙበታል።  

Kenia wartet mit Spannung auf das Urteil des Obersten Gerichtshofs zu den Wahlen | Richter
የኬንያ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ምስል Baz Ratner/REUTERS

«ይህን ሰዉ እዝያዉ እስር ቤት እያለ ነዉ እኔ የወጣሁት። ዳቦ ሰርቆ ነበር የታሰረዉ። አንድ ሰው እዚያው ጥዬው ሄድኩ ማለቴ ነው፣ አንድ ዳቦ በመስረቁ ነዉ የሞት ፍርድ ተበየነበት። 25 ሚሊዮን አይደለም። አንድ ዳቦ ነዉ። እና ሰዉየዉ 1996 ጀምሮ እስከዛሬ እስር ላይ ነዉ። » 

ባለፈው ዓመት ህዳር ወር የኬንያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በሃገሪቱ ምክትል ፕሬዝዳንት ሪጋቲ ጋቻጓ ላይ የተመሰረተዉን የ60 ሚሊዮን ዶላር የሙስና ቅሌት ክስ ዉድቅ አድርጎታል። ይህ ብቻ አይደለም ባለፈዉ ጥቅምት ወር መጀመሪያ ላይ የኬንያ አቃቤ ህግ ዳይሬክተር ኑርዲን ሃጂ አዲሱ የኬንያ ፕሬዝዳንት ወደ ስልጣን እንደመጡ በዊሊያም ሩቶ አጋሮች ላይ የተነጣጠረዉን የሙስና ቅሌት ክስ ሽረዋል። እነዚህ ክስ የተሻረላቸዉ ሰዎች አብዛኞቹ ተጠርጣሪዎች አሁን የፕሬዚዳንት ዊልያም ሩቶ የካቢኔ አባላት ናቸዉ።

የኬንያ የሰብአዊ መብት ኮሚሽን በአሁኑ ወቅት የሞት ቅጣትን በሃገሪቱ እንዲሻር ለማድረግ ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል። ምንም እንኳን የሞት ቅጣት አሁንም በኬንያ ህጋዊ ቢሆንም ወንጀልን በመዋጋት ረገድ ውጤታማ አለመሆኑን እና ድሆች ላይ ብቻ ማነጣጠሩን የኬንያ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን አጽኖት ሰጥቷል። በኬንያ የመጨረሻው የሞት ቅጣት የተበየነበት ሰው ከተገደለ 35 ዓመታት እንዳለፈዉም ከኬንያ የደረሰን ዘገባ ያመለክታል።   

አዜብ ታደሰ

ማንተጋፍቶት ስለሺ