1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኦፌኮ አቤቱታ

ማክሰኞ፣ ጥቅምት 10 2013

ዶ/ር ዳንኤል በቀለ ችግሩ መጠን-ሰፊ መሆኑ በኮሚሽኑ አቅም ሁሉንም ቦታ በአጭር ጊዜ ለመድረስ ውስንነት ገጥሞናል ብለዋል።ሆኖም ያለፍርድ ቤት ማዘዣ መታሰርንና የዋስትና መብታው ተጠብቆላቸው በፖሊስ ቁጥጥር ስር የሚቆዩት እስረኞችን በተመለከተ ከመንግስት አካላት ጋር በመነጋገር በርካቶች እንዲለቀቁ ያደረግነው ጥረት በተወሰነ መልኩ ተሳክቷል ብለዋል።

https://p.dw.com/p/3kBWr
Äthiopien Addis Abeba | Büro des "Oromo Federalist Congress"
ምስል Seyoum Getu/DW

የኦፌኮ አቤቱታ

በተለያዩ ጊዜያት የአመራር፣ የአባላትና ደጋፊዎች እስራትና እንግልት እንዲሁም የጽህፈት ቤቶች መዘጋት ይደርስብኛል የሚለው የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግሬስ (ኦፌኮ) ይህንኑ አቤቱታ ለኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን እና ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባቀርብም መልስ አልተሰጠኝም ብሏል።ፓርቲው በተለይም ለዶይቼ ቬለ እንዳስታወቀው ባለፈው ሰኔ ብቻ ከ90 በላይ ሰዎች ስም ዝርዝር የተጻፈበት የአባላት እስራት አቤቱታ ለኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን እና ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ቢያቀርብም ምላሽ አላገኘሁም ብሏል።በጉዳዩ ላይ አሰተያየታቸውን ለዶይቼ ቬለ የሰጡት የኢትዮጵያ ሰብዐዊ መብቶች ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ የችግሩ መጠን ሰፊ በመሆኑ በኮሚሽኑ አቅም ሁሉንም ቦታ በአጭር ጊዜ ለማዳረስ አለመቻሉን ተናግረዋል።ሆኖም ያለ ፍርድ ቤት ማዘዣ መታሰርንና የዋስትና መብታው ተጠብቆላቸው በፖሊስ ቁጥጥር ስር የሚቆዩት እስረኞችን በተመለከተ ከመንግስት አካላት ጋር በመነጋገር በርካቶች እንዲለቀቁ አደረግን ያሉት ጥረት በተወሰነ ደረጃ ተሳክቷል ብለዋል።የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ በርድ ቃል አቀባይ ሶሊያና ሽመልስ በበኩላቸው ፓርቲዎች በሚፅፉላቸው አቤቱታዎች መሰረት ከሚመለከታቸው ተቋማት ማብራሪያ እየጠየቁ መሆኑን ለዶቼ ቬሌ ገልፀዋል፡፡
ስዩም ጌቱ 
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ