1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኦነግ ወቀሳ

ዓርብ፣ የካቲት 6 2012

ቀድሞው አማፂ ቡድን ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ በጠራዉ ጋዜጣዊ ጉባኤ እንዳዉ የኢትዮጵያ መንግሥት ባገባደድነዉ ሳምንት ብቻ 400 የኦነግ አባላትና ደጋፊዎችን አስሯል።

https://p.dw.com/p/3XnM7
 Logo Oromo Liberation Front

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) አባላትና ደጋፊዎቹ በመንግሥት ፀጥታ አስከባሪዎች የእስራት ዘመቻ ተከፍቶባቸዋል በማለት ወቀሰ። የቀድሞው አማፂ ቡድን ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ በጠራዉ ጋዜጣዊ ጉባኤ እንዳዉ የኢትዮጵያ መንግሥት ባገባደድነዉ ሳምንት ብቻ 400 የኦነግ አባላትና ደጋፊዎችን አስሯል። የኦነግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል ሚካኤል ቦረን በተለይ ለዶቸ ቬለ በስልክ እንደገለጡት ደግሞ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ የዛሬ ሁለት ዓመት ግድም የገቡትን ቃል አጥፈው መንግሥታቸዉ የሰብአዊ መብቶችን እየጣሰ ነው።አቶ ሚካኤል እስካሁን ድረስ ጫካ የሸመቀዉ የኦነግ ታጣቂ ኃይል ወደ ሰላማዊ ትግል እንዳይመለስ እንቅፋት የሆነው የኢትዮጵያ መንግሥት ነው በማለት ይወቅሳሉ።ኦነግ ኢትዮጵያ ከገባበት ጊዜ ጀምሮ ሠላም ለማስፈን በተደጋጋሚ መጣሩንም አቶ ሚካኤል አስታዉቀዋል።ጥረቱን የሚያመለክትን አብነት ግን አልጠቀሱም።

ታምራት ዲንሳ

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሰ