1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኦነግ አመራሮች አቀባበል በመስቀል አደባባይ

ቅዳሜ፣ መስከረም 5 2011

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) አመራሮች ዛሬ በመስቀል አደባባይ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል። የኦነግ ሊቀመንበር አቶ ዳውድ ኢብሳን ጨምሮ የድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮች እኩለ ቀን ገደማ መስቀል አደባባይ ሲደርሱ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ደጋፊዎቻቸው በሆታ ተቀብለዋቸዋል።

https://p.dw.com/p/34vUT
Äthiopien Bevölkerung begrüßen OLF-Führungskräfte
ምስል DW/Y. Gebreegziabher

የኦነግ አመራሮች አቀባበል በመስቀል አደባባይ

ትላንት ለሊቱን እና ዛሬም እስከ እኩለ ቀን ድረስ የነበረውን ዝናብ ተቋቁሞ አቶ ዳውድን እና የተወሰኑ የኦነግ የሰራዊት አባላትን ለመቀበል ወደ መስቀል አደባባይ የተመመው የህዝብ ጎርፍ ጠጠር ቢወረወር መሬት የማያስጥል የሚሉት አይነት ነበር። የጸጥታ ሁኔታውም በፌደራል እና በአዲስ አበባ ፖሊሶች እንዲሁም በቄሮዎች ጠንካራ ጥበቃ ሲደረግ ነበር። በአቀባበል ስነ ስርዓቱ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ አቶ ታከለ ኡማ ንግግር አድርገዋል። 

አቶ ዳውድ ኢብሳም ሊቀበላቸው ለተሰበሰበው ህዝብ የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል። እርሳቸው በስፍራው ላይ ከመድረሳቸው አስቀድሞ የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ ስራ አስኪያጅ አቶ ጃዋር መሐመድ እና የኦፌኮ ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር ለህዝቡ ንግግር አድርገዋል። አቶ በቀለ ወደ መድረክ ከውጣታቸው በፊት በመኪናቸው ውስጥ ሆነው ሲያነቡ ተመልክተናል።  

የዛሬውን የአቀባበል ስነስርዓት በስፍራው ሆኖ የተከታተለው ዘጋቢያችን ዩሃንስ ገብረእግዚያብሔር ያጠናቀረውን ዝርዝር ዘገባ ለማድመጥ የድምጽ ማዕቀፉን ይጫኑ።  

ዩሃንስ ገብረእግዚያብሔር 

ተስፋለም ወልደየስ