1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኦስትርያዉ ምክር ቤታዊ ምርጫና ዉጤቱ

እሑድ፣ መስከረም 18 2012

የኦስትሪያ ወግ አጥባቂ ፓርቲ «ÖVP» መሪ ሰበስታያን ኩርዝ ፓርቲ እሁድ የተጠራዉን የምክር ቤት በአብላጫ ድምፅ አሸነፈ። የኦስትሪያዉ ወግ አጥባቂ ፓርቲ በምርጫዉ ያገኘዉ ዉጤት ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር ጥምር መንግሥት ለመመስረት እና ለመመምራት የሚያስችለዉ ነጥብ ማግኘቱ ታዉቋል።

https://p.dw.com/p/3QSLX
Österreich Wien Parlamentswahl Kurz
ምስል Getty Images/M. Gruber

የኦስትሪያወግአጥባቂ ፓርቲ መሪ ሰበስታያን ኩርዝ ፓርቲ ዛሬ እሁድ የተጠራዉን የምክር ቤት በአብላጫ ድምፅ አሸነፈ። የኦስትሪያዉ ወግ አጥባቂ ፓርቲ በምርጫዉ ያገኘዉ ዉጤት ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር ጥምር መንግሥት ለመመስረት እና ለመመምራት የሚያስችለዉ ነጥብ ማግኘቱ ታዉቋል። ወግ አጥባቂዉ የሰበስታያን ኩርዝ ፓርቲ   37.2% ያገኘ ሲሆን የሶሻል ዲሞክራቱ ፓርቲ 22.0%, ቀኝ ነፃ ፓርቲ  16.0% አረንጓዴዎች  14.3%  ማግኘታቸዉ ተዘግቦአል።  ኦስትሪያ ዛሬ በተካሄደዉ የፓርላማ ምርጫ 6,4 ሚሊዮን ሕዝብ  እንዲሳተፍ ጥሪ መደረጉ ተመልክቶአል።   የፓርላማ ምርጫ ለማካሄደ የበቃዉ፤ ባለፈዉ ግንቦት ወር የኦስትርያ ተጣማሪ  መንግሥት የወግ አጥባቂዉ ፓርቲ « ÖVP » እና  ቀኝ ክንፍ ፓርቲ « FPÖ»  ክፍፍል ገብቶ በመፍረሱ ነበር። የኦስትርያዉ ወግ አጥባቂዉ  « ÖVP » ፓርቲ የቀድሞ ፕሬዚደንት ለምርጫ ዘመቻ ድጋፍ የሚዉል ገንዘብን ከሩስያ ለመቀበል ሲያመቻቹ የሚያሳይ ቪዲዮ ተገኘ መባልን ተከትሎ ጥምሩ መንግስት መፍረሱም ተመልክቶአል። ኦስትርያ ምክር ቤት በሃገሪቱ መራሔ መንግሥት ሰበስትያን ኩርዝ ላይ ባሳለፈዉ የመተማመኛ ጥያቄ፤ በቂ ድምፅን ባለማግኘታቸዉ፤ ኦስትርያ ዳግም የፓርላማ ምርጫ እንድታደርግ መወሰኑ ይታወቃል።    

አዜብ ታደሰ 

እሸቴ በቀለ