1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኦሮሚያ  የሰዓት እላፊ ገደብ ማሻሻያ

ሐሙስ፣ ኅዳር 9 2014

የክልሉ መንግሥት ሕገወጥ እንቅስቃሴን ለመቆጣጠር በሚል በጣለዉ የሰዓት እላፊ ገደብ መሰረት፣ ሰዎች መንቀሳቀስ የሚችሉት ከማለዳዉ 11ሰዓት ተኩል እስከ ምሽቱ 3 ሰዓት፣ መኪኖች ደግሞ ከማለዳዉ 11ሰዓት ተኩል እስከ ምሽቱ 2 ሰዓት ብቻ ነበር።

https://p.dw.com/p/43C1s
Äthiopien Regionalstaat Oromia
ምስል Seyoum Getu/DW

የኦሮሚያ ክልል የሰዓት እላፊ ገደቡን አነሳ

የኦሮሚያ ክልል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ  ዕዝ በሰው እና በተሸከርካሪዎች ላይ ጥሎት የነበረዉን የሰዓት ዕላፊ ገደብ አነሳ። የክልሉ መንግሥት ሕገወጥ እንቅስቃሴን ለመቆጣጠር በሚል በጣለዉ የሰዓት እላፊ ገደብ መሰረት፣ ሰዎች መንቀሳቀስ የሚችሉት ከማለዳዉ 11ሰዓት ተኩል እስከ ምሽቱ 3 ሰዓት፣ መኪኖች ደግሞ ከማለዳዉ 11ሰዓት ተኩል እስከ ምሽቱ 2 ሰዓት ብቻ ነበር። የክልሉ አቃቤ ሕግ ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ግን ገደቡ መሻሻሉን አስታዉቋል።

ስዩም ጌቱ 

ነጋሽ መሐመድ

ኂሩት መለሰ