1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
እምነት

የኦሮሚያ ሚዲያ ማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ተጻፈበት

ሐሙስ፣ የካቲት 19 2012

የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ (OMN) የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ላይ ባስተላለፈው ዘገባ ማስተካከያ እንዲያደርግ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን በደብዳቤ ጠየቀ። የማስጠንቀቂያ ርምጃው ከመገናኛ ብዙኃን ጋር ያለ እለታዊ የመደጋገፍ እና የማረም አካል መሥሪያ ቤቱ ተናግሯል።

https://p.dw.com/p/3YWLN
Logo Oromia Media Network

«ከብዙኃን መገናኛ ሕግ እና ደንብ አኳያ በሕግ እንዲጠየቁ»

የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ (OMN) ስለ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ባስተላለፈው ዘገባ ማስተካከያ እንዲያደርግ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን በደብዳቤ ጠየቀ። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቅዱስ ሲኖዶስ ከየካቲት 9 እስከ 11 ቀን፤ 2012 ዓ.ም ካካሄደው አስቸኳይ ጉባኤ  በኋላ ባወጣው መግለጫ፣ የቤተክርስቲያኒቱን ስም ያጠፋሉ ባላቸው መገናኛ ብዙኃን ላይ መንግሥት አስፈላጊውን ውሳኔ እንዲያሳልፍ መጠየቁ ይታወሳል። ቅዱስ ሲኖዶሱ የስም ማጥፋት ዘመቻ በማካሄድ የቤተክርስቲያንን ታሪክ እያበላሹ ነው ካላቸው መገናኛ አውታሮች መካከል አንዱ ኦ ኤም ኤን የተባለው ጣቢያ መኾኑን ገልጦ፦ «ከብዙኃን መገናኛ ሕግ እና ደንብ አኳያ በሕግ እንዲጠየቁ»ም ብሎ ነበር። የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን ለዶይቸ ቬለ (DW)እንደገለጠው ግን ለኦኤምኤን የላከዉን ማስጠንቀቂያ  ከመገናኛ ብዙኃን ጋር ያለ እለታዊ «የመደጋገፍ እና የማረም አካል ነው» ብሏል። 


ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር 
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ነጋሽ መሐመድ
 

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር 
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ነጋሽ መሐመድ