1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኦርቶዶክስ አማኞች የተቃዉሞ ሠልፍ

ዓርብ፣ ኅዳር 26 2012

አዉሮጳ የሚኖሩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተወሕዶ ቤተ-ክርስቲያን መሪዎችና የእምነቱ ተከታዮች ኢትዮጵያ ዉስጥ በዕምነቱ ተከታዮችና በአብያተ ክርስቲያናት ላይ ይደርሳል ያሉትን ጥቃት በመቃወም የሚያደርጉት ያደባባይ ሰልፍ እንደቀጠለ ነዉ

https://p.dw.com/p/3UKID
Demo in Berlin
ምስል Yilma Hiz

የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ክርስቲያኖች ሰልፍ በበርሊን

አዉሮጳ የሚኖሩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተወሕዶ ቤተ-ክርስቲያን መሪዎችና የእምነቱ ተከታዮች ኢትዮጵያ ዉስጥ በዕምነቱ ተከታዮችና በአብያተ ክርስቲያናት ላይ ይደርሳል ያሉትን ጥቃት በመቃወም የሚያደርጉት ያደባባይ ሰልፍ እንደቀጠለ ነዉ።ባለፈዉ ሮብ ፈረንሳይ የሚኖሩ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን መሪዎችና ተከታዮች ባደረጉት ሠልፍ በእምነቱ ተካታዮችና ተቋማት ላይ የሚደርሰዉን ጥቃት የኢትዮጵያ መንግስት ያስቆም ዘንድ የፈረንሳይ መንግሥት ግፊት እንዲያደርግ ጠይቀዋል።ዛሬ ደግሞ ጀርመንና ቤልጂግ የሚኖሩ የኦርቶዶክስ አብያተ-ክርስቲያናት መሪዎችና ምዕመናን ተመሳሳይ ሰልፍ በማድረግ ተመሳሳይ ጥያቄ አቅርበዋል።የበርሊኑን ሠልፍ እዚያዉ በርሊን የሚገኘዉ ወኪላችን ይልማ ኃይለ ሚካኤል ተከታትሎት ነበር።ኂሩት መለሰ ይልማን በስልክ አነጋግራዋለች።ብራስልስ አዉሮጳ ሕብረት ፅሕፈት ቤት አጠገብ የተደረገዉን የአደባባይ ሰልፍ የተከታተለዉን የብራስልሱን ወኪላችን ገበያዉ ንጉሴን ደግሞ ዛሬ ዕኩለ ቀን በስልክ አነጋግሬዉ ነበር።

ይልማ ኃይለ ሚካኤል

ገበያዉ ንጉሴ

ነጋሽ መሐመድ

ኂሩት መለሰ

                              

 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ