1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

 የእነእስክንድር የፍርድ ሒደት

ረቡዕ፣ ጥር 26 2013

አመፅና ሁከትን በመቀስቀስ ወንጀል የተከሰሱትን የባልደራስ ለእዉነተኛ ዴሞክራሲ ሊቀመንበር የእስክንድር ነጋና አባሪ ተባባሪ የተባሉ ሌሎች ተከሳሾችን የክስ ሒደት የሚመረምረዉ ፍርድ ቤት ለዛሬ ይዞት የነበረዉን ቀጠሮ ሠረዘ።

https://p.dw.com/p/3oq5V
Symbolbild Gericht Gesetz Waage und Hammer
ምስል Fotolia/Sebastian Duda

«የችሎት ውሎ»

አመፅና ሁከትን በመቀስቀስ ወንጀል የተከሰሱትን የባልደራስ ለእዉነተኛ ዴሞክራሲ ሊቀመንበር የእስክንድር ነጋና በአባሪ ተባባሪነት የተጠረጠሩ ሌሎች ተከሳሾችን የክስ ሒደት የሚመረምረዉ ፍርድ ቤት ለዛሬ ይዞት የነበረዉን ቀጠሮ ሠረዘ። የኢትዮጵያ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሕገ-መንግሥትና የፀረ ሽብር ችሎት በእነእስክድር ነጋ መዝገብ በተከሰሱ ተጠርጣሪዎች ላይ ከሳሽ አቃቤ ሕግ ያስቆጠራቸዉን ምስክሮች ቃል ለመስማት ለዛሬ ቀጥሮ ነበር። ይሁንና አቃቤ ሕግ የምስክሮቹ ቃል በዝግ እንዲሰማ ለፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት አቤት በማለቱ ፍርድ ቤቱ አቤቱታዉን ተቀብሎ ምስክሮች የመስማት ሒደቱን በማገዱ ነዉ። ተከሳሾችና ጠበቆቻቸዉ የከፍተኛ ፍርድ ቤቱን ዉሳኔ ተቃዉመዉታል።

 ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር

ነጋሽ መሐመድ

ማንተጋፍቶት ስለሺ