1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የእስራኤል 70ኛ ዓመት ምስረታ ቤተ-እስራኤላዉያን

ረቡዕ፣ ሚያዝያ 10 2010

እስራኤል የተመሰረችበት 70ኛ ዓመት ነገ በይፋ እንደሚከበር ተገለፀ ። ነገ ከሚከበረዉ ይፋዊ የእስራኤል ምስረታ ቀደም ሲል የተለያዩ ዝግጅቶች የተደረጉ ሲሆን በተለያዩ ክስተቶች ለእስራኤል የተሰዉ ከ 23,000 የሚበልጡ እስራኤላዉያን ዛሬ በተለያዩ ዝግጅቶችና በሕሊና ፀሎት እየታሰቡ ነዉ።

https://p.dw.com/p/2wHRn
Israel Protest gegen Regierungspläne - Ausweisung afrikanischer Flüchtlinge
ምስል Reuters/C. Kern

«በተለያዩ ግዳጆች ለሃገሪቱ የተሰዉ ቤተ-እስራኤላዉያንም ታዉሰዋል»


በሺዎች በሚቆጠሩ በእስራኤል ከተሰዉት መካከል በአሸባሪ ጥቃትና በጥበቃ ስራ ላይ ሳሉ በደረሰ አደጋ የተሰዉ ቤተ-እስራኤላዉያንም ይገኙበታል። ዛሬ ሲደረግ የዋለዉ የመታሰብያ ሥነ-ስርዓት ምሽት ላይ የተሰዉ የእስራኤል ጀግኖችን በሚከብረዉ ችቦ ማብራት ስነስርዓት ይጠቃለላል። በነገዉ እለት በተለያዩ ትርዒቶች እንደሚከበር ተገልፆአል። በሌላ በኩል ሃገራችንን ወረዋል ሲሉ በሚከሱት ፍልስጤማዉያን ጥያቄ የእስራኤል ሰባኛ ዓመት ምስረታ ጥላ አጥልቶበት ይገኛል። በእስራኤል ስለ 70ኛ ዓመት ምስረታ ክብረ በዓል በተመለከተ በእስራኤል የቀድሞዉ የአፍሪቃ ስደተኞች ጉዳይ ቢሮ ዋና ተጠሪን አቶ ዮሃንስ ባዩን አነጋግረንናል። አቶ ዮሃንስ ስለሚታየዉ ድባበብ በመግለፅ ቃለ ምልልሱን ይጀምራሉ።   

አዜብ ታደሰ 
ነጋሽ መሐመድ