1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የእስልምና ጉዳዮችና የመስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ ተስማሙ

ረቡዕ፣ ሰኔ 27 2010

ሼህ መሐመድ አሚን ጀማል የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ጉባኤ ፕሬዝዳንት ሁለቱ ወገኖች በአጭር ጊዜ ውስጥ ስምምነት ላይ ሊደርሱ የቻሉት ሰላም እንዲወርድ በመፈለጋቸው መሆኑን ለዶቼቬለ ተናግረዋል።

https://p.dw.com/p/30qgZ
Screenshot Facebook Äthiopien
ምስል Facebook/Office of the Prime Minister-Ethiopia

ኢትዮጵያ የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት(መጅሊስ) እና የሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ ልዩነታቸውን ለማስወገድ እና በጋራ ለመሥራት ተስማሙ። የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አሕመድ ሁለቱን ወገኖች ከትናንት ወዲያ እና ትናንት በተናጠል እና በጋራ ካወያዩ በኋላ በርሳቸው ጥያቄ ይቅር ተባብለዋል፤ በጋራ ውይይት አካሂደውም ችግራቸውን ለማስወገድ የሚረዳ አንድ የጋራ ኮሚቴም አቋቁመዋል። ኮሚቴው ከሁለቱ ወገኖች እንዲሁም ከሀገር ሽማግሌዎች እና ከምሁራን የተውጣጡ 9 አባላት ይገኙበታል። ሼህ መሐመድ አሚን ጀማል የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ጉባኤ ፕሬዝዳንት ሁለቱ ወገኖች በአጭር ጊዜ ውስጥ ስምምነት ላይ ሊደርሱ የቻሉት ሰላም እንዲወርድ በመፈለጋቸው መሆኑን ለዶቼቬለ ተናግረዋል።ሼህ መሐመድ ሁለቱ ወገኖች ወደፊት ግንኙነታቸውን ይበልጥ ያጠናክራሉ የሚል እምነት አላቸው።ሁለቱ ወገኖች በጋራ ባካሄዱት ስብሰባ መጅሊሱ “ሕዝበ ሙስሊሙን በተገቢው መልኩ የሚወክል መሪ ተቋም እንዲሆን” ከስምምነት ላይ ደርሰዋል ተብሏል።

ኂሩት መለሠ

አዜብ ታደሰ