1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኤርትራው ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ የሩሲያ ጉብኝት አንድምታ

ሐሙስ፣ ግንቦት 24 2015

ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን ትላንት በሞስኮ ከፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ ሲገናኙ የኤርትራው መሪ በመጪው የአፍሪቃ ሩሲያ ጉባኤ እንዲታደሙ ጋብዘዋል። የኤርትራው ፕሬዝደንት በበኩላቸው ዓለም ከአንድ ልዕለ ኃያል ተጽዕኖ ነጻ ሆና የአገሮች እና ሕዝቦች ነጻነት እና ክብር የሚጠበቅበት ሥርዓት እንዲፈጠር ሩሲያ የበኩሏን አስተዋጽዖ እንድታደርግ ጠይቀዋል።

https://p.dw.com/p/4S4QL
Isaias Afwerki
ምስል Khalil Senosi/AP Photo/picture alliance

የኤርትራው ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ የሩሲያ ጉብኝት አንድምታ

የኤርትራው ፕረዝደንት ኢሳይያስ አፈወርቂ ፕሬዝዳንት ፑቲን ባቀረቡላቸው ግብዣ መሰረት ካለፈው ሰኞ ጀምሮ ከከፍተኛ ባለስልጣኖቻቸው ጋር የሩሲያ ፈዴሬሺንን ለአራት ቀናት በመጎብኘት ላይ ናቸው። ፕረዝዳንት ኢሳይያስ ከሁለት ሳምንት በፊት በቻይናው መሪ ፕሬዝዳንት ጂፒንግ እንደዚሁ ተጋብዘው ቻይናን መጎብኘታቸው የሚታወስ ሲሆን፤ አሁን ደግሞ በ32ኛ አመት የነጻነት በዓል ማግስት፤ በጦርነት ውስጥ ባለችውና ሌላዋ የአሜሪክ ባላንጣ በሆነችው ሩሲያ መሪ ፕሬዝዳንት ፑቲን ተጋብዘው ወደ ሞስኮ ማቅናታቸው ትንሿን አገር ኤርትራንና መሪዋን ፕረዝዳንት ኢሳይያስን  ትኩረት እንዲስቡ አድርጓቸዋል።፡

ሁለቱ መሪዎች፤ ከፍተኛ ባለስልጣኖቻቸው በተገኙበት ትናንት ባደረጉት ውይይት፤ በሁለትዮሽና አለማቀፍ ግንኙነቶች ላይ በጥልቀት መወያየትቸው ተገልጿል። ኤርትራ፤ ሩሲያ  በዩክሬን ጦርነት ምክኒያት በመንግስታቱ ድርጅት ጉባኤዎች እንድትወገዝ የቀረቡ የውሳኔ ሀሳቦችን በመቃወም ከሩሲያ ጎን ከቆሙት ጥቂት የአፍርካ አገሮች ተጠቃሽ መሆኗ የሚታወቅ ሲሆን፤ ፕሬዝዳንት ፑቲንም፤ የሁለቱ አገሮች ወዳጅነት እያደገና እየጠንከረ መሄዱን በማውሳት በመጪው ሀምሌ ወር ሩሲያ በምታስተናግደው የሩሲያና አፍሪክ ጉባኤ ፕሬዝዳንቱ እዲሳተፉ ጋብዘዋቸዋል።

የሩሲያ ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን
ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን ትላንት በሞስኮ ከኤርትራው ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ ሲገናኙ የኤርትራው መሪ በመጪው የአፍሪቃ ሩሲያ ጉባኤ እንዲታደሙ ጋብዘዋል። ፑቲን እንዳሉት ሁለቱ መሪዎች በርከት ያሉ ሥምምነቶች እንደሚፈራረሙ ይጠበቃል። ምስል Gavriil Grigorovvia/Kremlin/Sputnik via REUTERS

ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ በበኩላቸው ለቀረበላቸው ግብዣና መስተንግዶ አመስግነው፤ በቻይና ጉብኝታቸው እንዳደረጉት ሁሉ፤ አለማችን  ከአንድ ልዕለ ሀያል ተጽኖ ነጻ ሁና የአገሮችና ህዝቦች ነጻነትና ክብር የሚጠበቅበት አለማቀፋዊ ስራት እንዲፈጠር  ሩሲያ የበኩሏን አንድትወጣ ጥሪ ማስተላለፋቸው ተገልጿል።

በአሁኑ ወቅት፤ አሜሪክና አውሮፓ በአንድ ወገን፤ ሩሲያና ቻይና ቤላ ወገን ሆነው እይተሻኮቱ ባለበት ወቅት፤ ከአገራቸው ውጭ ብዙም በመጓዝ የማይታወቁት የትንሺቱ አገር መሪ ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ ወደ ቤጂንግና ሞስኮ የሚያደርጉት መመላለስ ብዙ መላ ምቶችን የሚያስነሳና የሚያወያይም ሁኗል።

በለንደን ኑዋሪ የሆኑት ኢርትራዊው ጸሀፊና የአፍርካ ቀንድ የፖለቲክ ተንታኝ አቶ አብዱርህማን ሰይድ የፕሬዝዳንት ኢሳይያስን ወደ ሩሲያና ቻይና ማዘንበል፤ ፕሬዝዳንት መንግስቱ በአብዮቱ መጀመሪያ አመታት አሚሪካኖቹ መሳሪያ አንሰጥም ሲሏቸው ከወሰዱት እሲርምጃ ጋር ያመሳስሉታል።ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ ቀድሞ በአሜርካኖቹ ከሚወደሱትና በወቅቱ የአፍርካ ተስፋዎች ይባሉ ክነበሩት መሪዎች አንዱ የነበሩ ቢሆንም፤ ወደ ሩሲያና ቻይና  የዞሩት ግን በኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ወቅት አሜሪካኖቹ  ከኢትዮጵያ በተለይም ከውሀትና መለስ ዘናዊ ጋር ሆነው እሳቸውን ስላገለሏቸውና ክብርም ስለነሱዋቸው እንደነበር ይናገራሉ። 

Karte Horn von Afrika Golfstaaten EN
ኤርትራ በጂኦግራፊያዊ አቀማመጧ ምክንያት የዓለም ልዕለ ኃያላን ቀልብ ከሚስቡ አገሮች መካከል ነች።

በቻይናን ሩሲያ በኩል ደግሞ በተለይ አሁን ከምዕባውያኑ ጋር ያለው ቅራኔ እየሰፋ ሲሄድ፤ እንደ ኤርትራ ያለች አቀማመጧ ከፍተኛ ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ ያለው አገር አስፈልጊያቸው ትሆናለች፤ የጦር ሰፈርም በመገንባት ሊጠቀሙባት ይችላሉ በማለት በተለይ ሩሲያኖች የኢርትራን ወደቦችና ስትራቴጂካዊ ቦታዎቿን በደንብ ያሚያቁዋቸው መሆኑን አንስተዋል።፡ ይሁን እንጂ ኤርትራ ለአሜሪክኖቹም ይሁን ለቻይና ወይም ለሩሲያ ስትራቴጂካዊ  ጠቀሚታ ያላት ቢሆንም፤ የሚታይ ድክመት ግን አለ ነው የሚሉት አቶ አብዱርህማን።

ከዚህ በተጨማሪም የሀይላኖቹ አገሮች ፍጥጫና በትንንሽ አገሮች ላይም የሚያደርጉት ሺሚያ የየአገሮቹንም ሰላም ሊያውክና እርስበርስም ሊያጋጭ ይችላል በማለት በቀዝቃዛው አለም ጦርነት ወቅት ይደረግ የነበረውን በማንሳት በአፍሪካ ቀንድ ላይ የሚደረገው ሺኩቻ በአክባቢው ሰላምና መረጋጋት ላይ አሉታዊ ተጽኖ ሊያሳድር ይችላልም ብለዋል።። ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ የሚያደርጉት የሚያበሳጫቸው ምዕራባውያንም አገራቸውን ኤርትራን ይልቁንም ወደሌላ ግጭት እንዳያስገባት የሚሰጉ መሆኑንም አቶ አብዱርህማን ለዲደብሊው በሰጡት አስተይየት አስታውቀዋል።

ገበያው ንጉሴ

እሸቴ በቀለ

ማንተጋፍቶት ስለሺ