1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኤልክትሪክ ገመዶችና ማስተላለፊያዎች የተቀናጀ ዘረፋ

ዓርብ፣ ግንቦት 19 2014

በ2013 በጀት ዓመት ብቻ በቀላል ባቡር መስመር ላይ በተዘረጋ የኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማቶች ላይ በተፈፀመ የስርቆት ወንጀል አንድ ሚሊዮን ብር የሚያወጡ የኤሌክትሪክ ገመዶች ስርቆት መፈጸሙ ተገለጠ። የኢትዮጵያ ኤልክትሪክ ኮርፖሬት ባለፈው አንድ ዓመት 1 ሚሊዮን 293 ሺህ 350 ብር የሚገመት የኤሌክትሪክ ገመድ ስርቆት እንደተፈፀመ ዐስታውቋል።

https://p.dw.com/p/4BxUQ
Addi Abeba Straßenbahn
ምስል DW/Y. Gebreegziabher

በሚሊዮን ብር የሚገመት የኤሌክትሪክ ገመድ ተሰርቋል

በ2013 በጀት ዓመት ብቻ በቀላል ባቡር መስመር ላይ በተዘረጋ የኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማቶች ላይ በተፈፀመ የስርቆት ወንጀል ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ የኤሌክትሪክ ገመዶች ስርቆት መፈጸሙ ተገለጠ። የኢትዮጵያ ኤልክትሪክ ኮርፖሬት ለዶይቸ ቬለ (DW) እንደተናገረው፦ ባለፈው አንድ ዓመት ብቻ 1 ሚሊዮን 293 ሺህ 350 ብር የሚገመት ርዝመቱ 1 ሺህ 55 ሜትር የሚደርስ የኤሌክትሪክ ገመድ (ኬብል) ስርቆት እንደተፈፀመ ዐስታውቋል። 

በሀገራችን ኤሊክትሪክን ለብርሀን ብቻ መጠቀም ከጀመርን ሰነባብተናል። አሌክትሪክ የሀገር ውስጥ እና ሀገር አቁዋራጭ ቀላል ከባድ የባቡር ትራንስፖር የስልክ የኔት ወርክ አገልግሎት እንና ለያንዳድንዱ እንቅስቃሴያችን መሰረት ያደረገው በዚሁ የአሌክትሪክ ኃይል ነው። የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በሀገሪቱ በሚሰጠው አቅርቦት ገና ተደራሽ ሆኖ ሳይጨርስ ካለችውም አቅርቦት በዘራፊዎች ተቸገርኩ ሲልተናግሯል።

በአዲስ አበባ፣ እና በተቅሩት የሀገሪቱ ክፍሎች የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶች ላይ የሚፈፀመው የስርቆት ወንጀል አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን ኪሳራውም ከአቅም በላይ እየሆነ መምጣቱን አቶ መላኩ ታዪ የኢትዮጵያ አሌክትሪክ አገልግሎት የኮርፖሬት ኮምኒኬሽን  ኃላፊ ለዶይቸ ቬለ (DW) ዐስታውቀዋል። 

Addi Abeba Straßenbahn
ምስል DW/Y. Gebreegziabher

የሕዝብ ግኝኙነቱ እንዳሉት የኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል አገልግሎት  ኤሌክትሪክ እንደከዚህ ቀደሙ የሚጠቀመው ለመብራት ብቻ አይደለም ዛሬ ሁሉም በሀገሪቱ የሚንቀሳቀሱ መመሰረተ-ልማቶች  በሙሉ በአንድም በሌላም መልኩ የኤሌክትሪክ ኃይልን ይጠቀማሉ። በመሆኑም በእነኘህ ኃላፊነት በጎደላቸው ስግብግብ ግለሰቦች የሚደረገው ዘረፋ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይልን ብቻ ሳይሆን፤ ሌሎችንም አገልግሎቱን የሚጠቀሙ ተቁዋማትን ላኪሳራ ይዳርጋል። በዚህም ኅብረተሰቡ የሚገባውን አገልግሎት እንዳያገኝ ሀገርም እንዳታድግ ያደርጋል ብለዋል። 

በተለይ የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ለባቡር በተዘረጉ የኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማቶች ላይ የሚፈፀመው የስርቆት ወንጀል የሃገርን ኢኮኖሚ ወደኋላ ከማስቀረቱም በተጨማሪ በከተማዋ ያለውን የባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት እያስተጓጎለ መሆኑን ተናግረዋል። 

በአጠቃላይ ከ2013 ዓ.ም ጀምሮ እስካሁን ድረስ 16 ሺህ 402 ሜትር የሚረዝም የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ ኬብል ስርቆት መፈፅሙን የተናገሩት ኃላፊው ተቁዋሙ በየግዜው ከለጋሽ ሀገሮች እና ከመንግስት በሚያገኘው ድጎማ የኃይል አቅርቦቱን ላማዳረስ እና ለማዘመን ቢሰራም ከአቅሙ በላይ በሆኑ ዘራፊዎች እስካሁን ከ26 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ኪሳራ ደርሶብኛል ይላል።
DW ያነጋገራቸው የአዲስ አበባ የቀላል ባቡር ተገልጋዮች ባቡሩ እንደልብ ቶሎ ቶሎ ባናገኘውም ያለውን የከተማ ትራንስፖርት ችግር አቃሎልናል ይላሉ። በዚህም መሰናክሎችዋ የበዙት የሀገሪቱ ዋና መዲና አዲስ አበባ የኤሊክትሪክ ሀይል አቅርቦት መቆራረጡ እንዳ ለቢሆንም ብርሀን በፈረቃ ከማግኘት ፋታ ካገኘች ሰንብታለች።

ሐና ደምሴ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ሸዋዬ ለገሰ