1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኤሌክትሪክ መቋረጥ በኢትዮጵያ 

ማክሰኞ፣ ሚያዝያ 23 2010

በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች ትናንት ማምሻውን የኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጡ ተሰምቷል። ዝቅተኛ ገቢ ከሚያስገኙ ሥራዎች አንስቶ፤ እስከ ብረታ ብረት መገጣጠሚያ እና ሌሎች የሞያ መስኮች ላይ የተሰማሩ ተጠቃሚዎች በኤሌክትሪክ ኃይል ተደጋጋሚ መቋረጥ መማረራቸውን ለዶይቸ ቬለ ተናግረዋል።

https://p.dw.com/p/2wyBi
Äthiopien Gide III Staudamm
ምስል Getty Images/AFP

በኤሌክትሪ መቆራረጡ ነዋሪዎች ተማረዋል

በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች ትናንት ማምሻውን የኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጡ ተሰምቷል። ዝቅተኛ ገቢ ከሚያስገኙ ሥራዎች አንስቶ፤ እስከ ብረታ ብረት መገጣጠሚያ እና ሌሎች የሞያ መስኮች ላይ የተሰማሩ ተጠቃሚዎች በኤሌክትሪክ ኃይል ተደጋጋሚ መቋረጥ መማረራቸውን ለዶይቸ ቬለ ተናግረዋል። በተለይ ትናንት ምሽት በመላ ሃገሪቱ በሚገኙ የተለያዩ አካባቢዎች የኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጡ ተዘግቧል። 

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የውጭ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ምስክር ነጋሽን በመጥቀስ የመንግሥት መገናኛ ብዙኃን ችግሩን ለመፍታት «ርብርብ እየተደረገ» መኾኑን የሚገልጡ እና  «የኃይል መቋረጡ ተስተካክሏል» የሚሉ እርስ በእርስ በእርስ የተጣረሱ ዘገባዎችን ዛሬ በድረ-ገጻቸው አውጥተዋል።

ሙሉ ዘገባው ከታች የድምጽ ማዕቀፉ ውስጥ ይገኛል።

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ማንተጋፍቶት ስለሺ
አርያም ተክሌ