1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በመላ ሃገሪቱ ተከበረ

ሰኞ፣ ታኅሣሥ 29 2011

የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት (ገና) በዓል በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በመላ ኢትዮጵያ በድምቀት ተከብሮአል እየተከበረም ነዉ። በአገር ዉስጥና በዉጭ በሚገኙ ኢትዮጵያዉያን ዘንድ ከዋዜማው ጀምሮ በተለያዩ ሃይማኖታዊ ሥነ- ስርዓቶች በመከበር ላይ ባለዉ የገና በዓል ወቅት ዜጎች የተቸገሩ ሲረዱ፣

https://p.dw.com/p/3B9Rt
Israel Jerusalem Äthiopisch-Orthodoxe Zeremonie
ምስል Getty Images/AFP/M. Kahana

ሁሉም ለሀገር አንድነት እና ሰላም እንዲተጋ ጥሪ ተደርጓል

በጋራ ሲበሉና ሲጠጡ መዋላቸዉ ተገልፆአል። የሃይማኖት መሪዎች በዓሉን አስመልክቶ ባስተላለፉት መልዕክት፥ የክርስትና እምነት ተከታዮች ከሌሎች እምነት ተከታዮች ጋር በመተባበር ለሀገር ሰላም በተጠናከረ መልኩ እንዲሰሩ ጥሪ ማቅረባቸዉ ተገልፆአል።  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን፣ የኢትዮጵያ ካቶሊካውያን ቤተክርስቲያን እና የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነኢየሱስ፥ ለእምነቱ ተከታዮች ባስተላለፉት መልእክት ሁሉም ለሀገር አንድነት እና ሰላም እንዲተጋ ጥሪ ማስተላለፋቸዉም ተገልፆአል።  


ጌታቸዉ ተድላ ሃይለጌዮርጊስ


አዜብ ታደሰ 
አርያም ተክሌ