1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢዜማ፤ ኦፌኮ እና የትዴፓ የፖለቲካ ክርክር መድረክ  

ዓርብ፣ ሚያዝያ 15 2013

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ ፓርቲ መሪ ፤ ፕሮፌሰር መራራ ጉዲና የኦሮሞ ሕዝቦች ፊደራሊስት ኮንግረስ ፕሬዚደንት እና ዶ/ር አረጋዊ በርሄ የትግራይ ዴሞክራስያዊ ፓርቲ ፕሬዚደንት የተካፈሉበት ዉይይት እና ክርክር ከትናንት በስትያ ረቡዕ በበይነ መረብ ተካሂዶአል።

https://p.dw.com/p/3sUor
Karte Ethiopia und Eritrea ENG

«የኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ ጥያቄ ዉስጥ የሚከት ነዉ»

ድልድይ በአዉሮጳ ኢትዮጵያዉያን መድረክ ምርጫ 2013 በፖለቲካ ፓርቲዎች እይታ በሚል ርዕስ ያዘጋጀዉን እና ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ ፓርቲ መሪ ፤ ፕሮፌሰር መራራ ጉዲና የኦሮሞ ሕዝቦች ፊደራሊስት ኮንግረስ ፕሬዚደንት እና ዶ/ር አረጋዊ በርሄ የትግራይ ዴሞክራስያዊ ፓርቲ ፕሬዚደንት የተካፈሉበት ዉይይት እና ክርክር ከትናንት በስትያ ረቡዕ በበይነ መረብ ተካሂዶአል። ሦስቱ የፓርቲ መሪዎች ባደረጉዋቸዉ የመግብያ ንግግሮች ኢትዮጵያ አሁን ያለችበት ሁኔታ አስቸጋሪ እና የለዉጡን ሂደት ስኬትም ሆነ የሃገሪቱን አንድነት እና ሉዓላዊነት ጥያቄ ዉስጥ የሚያስገባ እንደሆነ ገልፀዋል።  

ገበያዉ ንጉሴ

አዜብ ታደሰ

እሸቴ በቀለ