የሲዳማ ክስተትን ተከትሎ የኢዜማ መግለጫ
ረቡዕ፣ ሐምሌ 17 2011ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) በሲዳማ ዞን "ኢመደበኛ" ባላቸዉ ቡድኖች በዜጎች ላይ ጉዳት ሲደርስ ግፊት ያደረጉ ኃይሎች ለደረሰዉ መጠነ ሰፊ ጉዳት ኃላፊነት ሊወስዱ ይገባል አለ። የድርጅቱ የሥራ ኃላፊዎች ዛሬ በሰጡት መግለጫ መንግሥት በአጥፊዎቹ ላይ "ጠንካራ ርምጃ" እንዲወስድ እንዲሁም ሰላማዊ ዜጎችን ከጥቃት እንዲከላከል ጠይቋል። ፓርቲዉ የዜጎች የመብት ጥያቄ በዘላቂነት የሚፈታዉ በሠላማዊ መንገድ ብቻ ነዉ ብሎአል። "በአሁኑ ወቅት ከተለያዩ ፖለቲካዊ ክስተቶች እና ግጭቶች ጋር ተያይዞ በወንጀል ተጠርጥረው የሚታሰሩ ዜጎች ቁጥር እየጨመረ መጥቷል" ያለው ኢዜማ "አልፎ አልፎ የኢዜማ አባላትም የእስሩ ሰለባ ሆነዋል" ሲል በመግለጫው ጠቁሟል። በወንጀል የተጠረጠሩ ሕግ ፊት መቅረባቸዉ ተገቢ መሆኑን ብናምንም ፤ ተጠርጣሪዎች ከመታሰራቸዉ በፊት ለእስር የሚያበቃ በቂ ምክንያት አለበት ሲል ባወጣዉ መግለጫ አሳስቧል። የአዲስ አበባዉ ወኪላችን መግለጫዉን ተከታትሎ ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል።
ዮሃንስ ገብረ እግዚአብሔር
አዜብ ታደሰ
ተስፋለም ወልደየስ