1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢንጅንየር ስመኘው በቀለ ሞት ላይ የፖሊስ ኮሚሽነር  መግለጫ

ዓርብ፣ ሐምሌ 20 2010

የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ስመኘው በቀለ ዛሬ በአዲስ አበባ መሥቀል አደባባይ መሞታቸውን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ዘይኑ ጀማል ገለጹ። ኮሚሽነር ዘይኑ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፣ ፖሊስ ኢንጅንየሩ በሞቱበት ቦታ የነበሩ ማስረጃዎች እና መረጃዎችን የሚሰጡ ሰዎችን ይዞ እየመረመረ ነው ብለዋል።

https://p.dw.com/p/328Uv
Äthiopien, Simegnew Bekele, Projektleiter des Grand Ethiopian Renaissance Dam (GERD)
ምስል DW/T.Waldyes

«የአሟሟታቸውን ሁኔታ የሚያሳይ የምርመራ ውጤት ፈጥነን ለማቅረብ ርብርብ እያደረግን ነው።»

ካለፈው ሰባት ዓመታት ወዲህ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዋና ስራ አስኪያጅ ሆነው ፕሮጀክቱን ሲመሩ የነበሩት የ57 ዓመቱ ኢንጅነር ስመኘው በቀለ በጥይት ተመተው ሕይወታቸው ማለፏን ነው ኮሚሽነሩ የገለጹት።

ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር

አርያም ተክሌ

ነጋሽ መሀመድ