1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢንዱስትሪ ፓርክ በድሬደዋ

ዓርብ፣ ጥቅምት 20 2013

በድሬደዋ  ከተማ  ትናንት ለበርካቶች የሥራ ዕድል ለመፍጠር ያስችላል የተባለ የኢንዱስትሪ  ፓርክ ተመርቋል። ግንባታው ከአራት ዓመት በፊት መጀመሩ የተገለጸው  ይኸው የኢንዱስትሪ ፓርክ ሙሉ በሙሉ ወደ ሥራ ሲገባ 40 ሺህ ዜጎች የሥራ ዕድል ሊያገኙ እንደሚችሉ ነው የተገለጸው። 

https://p.dw.com/p/3kf8F
Stadt Dire Dawa in Äthiopien
ምስል Hailegzi Mehari

«ሙሉ በሙሉ ሥራ ሲጀምር ለ40 ሺህዎች የሥራ ዕድል ይፈጥራል»

በድሬደዋ  ከተማ  ትናንት ለበርካቶች የሥራ ዕድል ለመፍጠር ያስችላል የተባለ የኢንዱስትሪ  ፓርክ ተመርቋል። ግንባታው ከአራት ዓመት በፊት መጀመሩ የተገለጸው  ይኸው የኢንዱስትሪ ፓርክ ሙሉ በሙሉ ወደ ሥራ ሲገባ 40 ሺህ ዜጎች የሥራ ዕድል ሊያገኙ እንደሚችሉ ነው የተገለጸው።  የኢንዱስትሪ ፓርኩን መርቀው የከፈቱት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከዚህ ቀደም እናቶች እና ሕጻናት ተቸግረው ባዩባት ድሬደዋ እንዲህ ያለው መሠረተ ልማት ተገንብቶ ለመመረቅ መገኘታቸው የፈጠረባቸውን ስሜት በወቅቱ  ገልጸዋል። ድሬደዋ ለጅቡቲ ወደብ ያለው ቅርበትም ሆነ ከግዛቲቱ ጋር የሚገናኝበት የባቡር መሥመር መኖሩ፤ ኅብረተሰቡብ ያለው የንግድ ግንዛቤ ተዳምሮ ሲታይ ኢንዱስትሪ ፓርኩ በተገቢው ቦታ የተቀመጠ ሊባል እንደሚችልም አመልክተዋል።  መሳይ ተክሉ ከድሬደዋ ዝርዝሩን ልኮልናል።

 መሳይ ተክሉ

ሸዋዬ ለገሠ

ማንተጋፍቶት ስለሺ