1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያውያን እስራኤላዉያን ተቃውሞ 

ሐሙስ፣ ሰኔ 27 2011

የተቃውሞው አስተባባሪዎች ስለቀጣይ እንቅስቃሴው በጽሑፍ ማሰራጨታቸው  የተገለፀ ሲሆን፣ ትናንት ማምሻውን አደባባይ ከወጡ ተቃዋሚዎች ቢያንስ ሰባቱ መታሰራቸው ተዘግቧል

https://p.dw.com/p/3LZuI
Israel Protest von äthiopischen Juden in Tel Aviv
ምስል Getty Images/AFP/A. Gharabli

የኢትዮጵያዉያን እስራኤላዉያን ተቃዉሞ

       
እስራኤል ውስጥ አንድ ኢትዮጵያዊ እስራኤላዊ ወጣት በፖሊስ እጅ  መገደሉ ያስቆጣዉ ሕዝብ ባለፈዉ ዕሁድ የጀመረዉ ያደባባይ ተቃዉሞና ዉግዘት ዛሬም አልሰከነም። በተለያዩ የእስራኤል ከተሞች ዋና ዋና መንገዶችን በመዝጋት እና ተሽከርካሪዎችን ጎማዎችን በማቃጠል የሚደረገዉ ተቃውሞ የሀገሪቱን መንግሥት ብቻ ሳይሆን ዓለም አቀፍ ትኩረትን ስቧል። የተቃውሞው አስተባባሪዎች ስለቀጣይ እንቅስቃሴው በጽሑፍ ማሰራጨታቸው  የተገለፀ ሲሆን፣ ትናንት ማምሻውን አደባባይ ከወጡ ተቃዋሚዎች ቢያንስ ሰባቱ መታሰራቸው ተዘግቧል። እስካሁንም የታሰሩትን ቁጥር 140 ያደርሰዋል። የሟቹ አባት ፤ አመፅ ያልተቀላቀለበት  ተቃውሞ እንዲቀጥል ማሳሰባቸው ተነግሯል። ኢየሩሳሌም የሚገኘው ጋዜጠኛ ዜናነህ መኮንን እንዲህ ያለው ድርጊት ተቃውሞ ሲያስነሳ የመጀመሪያ እንዳልሆነ ይናገራል። ዜናነህ እንደሚለው በተለይ እዚያው የተወለዱት ኢትዮጵያዉያን እስራኤላዉያን ወጣቶች የሚሰጡት ምላሽ ጠንከር ያለ ነው። ዜናነህን ሸዋዬ ለገሠ አነጋግራዋለች። ስለተቃውሞው በሚገልፀው ይጀምራል፤

ዜናነሕ መኮንን

ሸዋዬ ለገሰ

ኂሩት መለሰ