1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያና ሱዳን ምሁራን ስለ ድንበር ውዝግብ ተወያዩ

ዓርብ፣ የካቲት 5 2013

ኢትዮጵያጵ እና ሱዳንን በሚያወዛግበው የድንበር ጉዳይ የኢትዮጵያ እና የሱዳን ምሁራን ባህርዳር ከተማ ውስጥ ተገናኝተው መክረዋል። የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ምሁራን ከሱዳኑ የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ አቻዎቻቸው ጋር መምከር ጀምረዋል።

https://p.dw.com/p/3pHW4
Ethio Sudan Intellektuellen Konferenz Bahrdar
ምስል Alemnew Mekonnen/DW

ምሁራኑ የህዝብ ለሕዝብ ችግር አይደም ብለዋል

በሱዳንና በኢትዮጰያ መካከል የተፈጠረውን የድንበር ውዝግብ በሰላማዊ መንገድ ብቻ መፍታት የሁለቱን አገሮች የቆየ ግንኙነት ሳያላላ እንደሚያስቀጥል ምሁራን አመለከቱ። ሱዳናዊያን ምሁራንም ችግሮች ከመባባሳቸው በፊት የሁለቱ አገሮች መንግስታት ችግሮቻቸውን ሳይዘገዩ በመነጋገር መፍታት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ አስተባባሪነት በተካሄደው ውይይት ላይ ምሁራኑ እንዳሉት በአፍሪቃ አገሮች ያሉ የአገራት ድንበሮች የተሰመሩት በቅኝ ገዢዎች በመሆኑ የዚህ ዓይነት ውዝግብ በኢትዮጵያና በሱዳን መካከል ብቻ የተፈጠረ አዲስ ነገር አይደለም፣ ችግሩንም የህዝብ ማስመሰል ጠቃሚ እንዳልሆነ ነው የሚናገሩት፡፡

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የአፍሪቃ ታሪክ ረዳት ፕሮፌሰር ዶ/ር አይቸግረው አደራ እንደሚሉት በሁለቱ አገሮች ያልተፈቱ ብዙ ችግሮች ቢኖሩም በውይይት መፈታት ይኖርባቸዋል፡፡ ሱዳናውያን ምሁራን ይህን በሚገባ እንደሚገነዘቡና ለመፍትሔው እንደሚሰሩ መረዳታቸውንም ደ/ር አይቸግረው ተናግረዋል፡፡

የ3ኛ ዲግሪያቸውን በኢትዮ ሱዳን ደንበር ላይ ያጠኑትና በወሎ ዩኒቨርሲት የታሪክና ቅርስ አስተዳደር መምህር ዶ/ር ዓለማየሁ እርቅይሁን እንዳሉት፦ ሱዳን ሁልጊዜም ኢትዮጵያ ችግር ሲያጋጥማት ተመሳሳይ የጠባ ጫሪነት ባሕሪ ታሳያለች፤  ግን ይህ ብዙ መንገድ አያስኬድም ብለዋል፡፡

ሁለቱም አገሮች ችግሮቻቸውን ወደ ሦስተኛ ወገን ሳያሻግሩ በራሳቸው መንገድ መፍታት እንዳለባቸውና ይህ ደግሞ መሆን ያለበት ሱዳን አሁን የያዘቻቸውን ቦታዎች ስትለቅቅ ብቻ ነው ነው ያሉት ዶ/ር ዓለማየሁ፡፡

Karte Sudan Äthiopien EN

በሱዳን የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የስነጥበባት ፕሮፌሰር ኡመር አል አሚን በበኩላቸው በሱዳን ወታደራዊ ክንፉን ያካተተ የሽግግር መንግስት ከሶስት ዓመት በፊት ቢቋቋምም ወታደሩ ጦርነትን ይፈልጋል፣ የህዝቡ ፍላጎት ግን አይደለም፡፡ «የሱዳን መንግስት ወታደራዊ ክንፍ ግጭቱ እንዲቀጥል ይፈልጋል ህዝቡ ግን ይህን አይፈልግም።»
ቀጠናው የግጭት አካባቢ መሆን እንደሌለበትም ምሁሩ አመልክተዋል፡፡ «ይህ ቦታ የትብብር እንጂ የጦርነት መሆን የለበትም፣አሁን ኢትዮጵያ በትግራይ ያለውን የህግ ማስከበር ስላጠናቀቀች፣ ሁለቱ መንግስታት ችግሮቻቸውን በጠረጴዛ ዙሪያ በውይይት መፍታት ይጠበቅባቸዋል።»

የተፈጠረው ችግር የሁለቱ አገሮች ህዝቦች ችግር እንዳልሆነ ያመለከቱት ፕሮፌሰር ኡመር በሱዳን ገላባትና በኢትዮጵያ መተማ ከተሞች ያሉ ነዋሪዎች ይገበያያሉ፣ ከአዲስ ካርቱም ያለ ትራንስፖርትም እንደቀጠለ ነው፡፡ «ከአዲስ አበባ ካርቱምና ከካርቱም አዲስ አበባ በየቀኑ 5፣ 5 የህዝብ አውቶቡሶች ይመላለሳሉ፣ ከሱዳን ነዳጅ ይገዛል ከኢትዮጵያ ደግሞ ቡናና ጥራጥሬ ይሸመታል።»

ከጥቅምት መጨረሻጀምሮ ሱዳን የኢትዮጵያ መንግስት በትግራይ ሲያደርግ የነበረውን ህግ የማስከበር ዘመቻ ተከትሎ በምዕራብ ኢትዮጵያ ድንበር ተሸግራ ወረራ ፈፅማለች፡፡

ዓለምነው መኮንን

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ነጋሽ መሐመድ