የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሳምንታዊ መግለጫ
ሐሙስ፣ የካቲት 17 2014ማስታወቂያ
የአሜሪካ ምክር ቤት ኢትዮጵያን አስመልክቶ ዐዲስ ያወጣው ኤች አር 6600 የተባለው ረቂቅ ሕግ ኢትዮጵያ ምላሽ የሰጠችባቸውን ጥያቄዎች የሚያነሳ እና የራሳቸውን ፍላጎት ለማሳካት የተረቀቀ ነው ሲል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለፀ። ረቂስ ሕጉ ከሰብዓዊ መብት ጥሰት ምርመራ ፣ ከሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦት እንቅፋት መሆን ጋር በተገናኙ ጉዳዮች ላይ ኢትዮጵያን ተጠያቂ ለማድረግ የተረቀቀ መሆኑ ተሰምቷል።በሌላ በኩል የሚኒስቴሩ ቃል ዐቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ዛሬ በሰጡት መግለጫ በብራሰልሱ የአፍሪቃ - አውሮጳ ሕብረቶች ጉባኤ ላይ የተሳተፈችው ኢትዮጵያ ከየአገራቱ ጋር የሁለትዮሽ የተናጠል ፍሬያማ ውይይቶችን እንድታካሂድ እድል እንደፈጠረላት ተናግረዋል።
ሰሎሞን ሙጬ
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ