1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ ዉስጥ ሰብአዊ መብት እንዲከበር የሚጠይቀዉ ረቂቅ ፀደቀ 

ረቡዕ፣ ሚያዝያ 3 2010

የአሜሪካ ኮንግረስ «ምክር ቤት» በኢትዮጵያ ያለውን የሰብዓዊ መብት እና የዲሞክራሲ ጉዳዮችን የሚመለከተውን ኤች አር 128 ተብሎ የሚታወቀውን የውሳኔ ሀሳብ ትላንት ለዛሬ አጥብያ አጸደቀ፡፡ የውሳኔ ሀሳቡ በኢትዮጵያ የተፈጸሙ ግድያዎች እንዲጣሩ፣ የታሰሩ እንዲፈቱ፣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲነሳ እና አፋኝ የተባሉ ሕግጋት እንዲሻሩ ይጠይቃል፡፡

https://p.dw.com/p/2vsna
USA Kapitol in Washington
ምስል picture-alliance/dpa/A. Shelley

ኢትዮጵያ የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች በገለልተኛ አካላት እንዲጣሩጥሪ አቅርቧል።

 

ከዚህም በተጨማሪ በኢትዮጵያ የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች በገለልተኛ አካላት እንዲጣሩ እና ድርጊቱን ፈጽመዋል የተባሉ ሰዎችም ለህግ እንዲቀርቡ ጥሪ አቅርቧል፡፡ የውሳኔ ሀሳቡ የመብት ጥሰት ፈጽመዋል የተባሉ ግለሰቦች እና ተቋማት ላይም ማዕቀብ እንዲጣል ይሻል፡፡ የውሳኔ ሀሳቡ እንዳይጸድቅ የኢትዮጵያ መንግስት ግፊት ሲያደርግ መቆየቱ ይታወሳል፡፡ ከብዙ ማግባባት እና ግፊት በአሜሪካ ኮንግረስ የጸደቀው የውሳኔ ሀሳብ በኢትዮጵያ የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች በገለልተኛ አካላት እንዲጣሩ እና ድርጊቱን ፈጽመዋል የተባሉ ሰዎችም ለህግ እንዲቀርቡ ጥሪ አቅርቧል፡፡ የውሳኔ ሀሳቡ የመብት ጥሰት ፈጽመዋል የተባሉ ግለሰቦች እና ተቋማት ላይም ማዕቀብ እንዲጣል ይሻል፡፡ዝርዝሩን የዋሽንግተኑ ወኪላችን መክብብ ሸዋ ልኮልናል። 
መክብብ ሸዋ
አዜብ ታደሰ 
ሂሩት መለሰ