1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ ክፍላተ-ሃገራት ኅብረት ዓላማውን ይፋ አደረገ

ማክሰኞ፣ መጋቢት 10 2011

የኢትዮጵያ ክፍላተ-ሃገራት ኅብረት ኢትዮጵያን የሚመለከት ዐሥር ነጥቦችን አንጥሮ በማውጣት የጋራ ዓላማዎቹን ይፋ አደረገ። ኅብረቱ የጎሣ ፖለቲካ እና ጎሠኝነት ከስሞ አንድነት እንዲጠናከር አበክሮ እንደሚሠራ ገልጧል።

https://p.dw.com/p/3FJlJ
Union Äthiopischer Provinzen
ምስል DW/G. Tedla

የጎሣ ፖለቲካ እና ጎሠኝነት እንዲከስም አበክሮ እንደሚሠራ ገልጧል

የኢትዮጵያ ክፍላተ-ሃገራት ኅብረት ኢትዮጵያን የሚመለከት ዐሥር ነጥቦችን አንጥሮ በማውጣት የጋራ ዓላማዎቹን ይፋ አደረገ። ኅብረቱ የጎሣ ፖለቲካ እና ጎሠኝነት ከስሞ አንድነት እንዲጠናከር አበክሮ እንደሚሠራ ገልጧል። ከሦስት ሳምንት በፊት ከ25 ፓርቲዎች መካከል 21ዱ ተገኝተው ከተወያዩ በኋላ በዐሥሩ ነጥቦች  የተስማሙበት መሆኑን ኅብረቱ ዐስታውቋል።  ኅብረቱ ዘመኑ የኢትዮጵያም ኾነ የአፍሪቃ ሕዝቦች ይቀላቀላሉ የሚባልበት መኾኑን አጽንኦት በመስጠት፦ «የኤርትራን የማቀላቀሉ ጉዳይ የሚከብድ አይደለም» ብሏል። የኢትዮጵያ ክፍላተ-ሃገራት ኅብረት አመራርን የአዲስ አበባው ወኪላችን ጌታቸው ተድላ ኃይለ-ጊዮርጊስ አነጋግሮ ቀጣዩን ዘገባ ልኮልናል። 
ጌታቸው ተድላ ኃይለ-ጊዮርጊስ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
አዜብ ታደሰ