ኤኮኖሚ
የኢትዮጵያ እና ዩናይትድ ኪንግደም የንግድና መዋዕለ ንዋይ መድረክ
ማክሰኞ፣ ጥቅምት 6 2011ማስታወቂያ
ጠቅላይ ምኒስትር ዐብይ አሕመድ እና መንግሥታቸው የማሻሻያ እርምጃ መውሰዳቸውን እንደሚቀጥሉ አቶ አርከበ ዕቁባይ በለንደን በመካሔድ ላይ በሚገኘው የንግድ እና የመዋዕለ-ንዋይ የምክክር መድረክ ተናገሩ። በለንደን ከተማ በዛሬው ዕለት በተካሔደው የኢትዮጵያ እና የዩናይትድ ኪንግደም አመታዊ የንግድ እና የመዋዕለ ንዋይ የምክክር መድረክ ሁሉም የሥራ ዘርፎች ለንግድ ክፍት መሆናቸው የጠቅላይ ምኒስትሩ ልዩ የኤኮኖሚ አማካሪ ተናግረዋል። በውይይት መድረኩ በዶ/ር አርከበ ዕቁባይ የተመራው የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን ከ30 ኩባንያዎች ጋር ተሳትፏል። የለንደኗ ወኪላችን ሐና ደምሴ መድረኩን ተከታትላ የሚከተለውን ዘገባ አቀብላናለች።
ሐና ደምሴ
ሸዋዬ ለገሠ