1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የእርቅ ዳስ

ማክሰኞ፣ ታኅሣሥ 14 2012

በህወኃት እና በኤርትራው ገዥ ድርጅት ህዝባዊ ግንባር ንዲሞክራሲን ፍትህን ( ህግዴፍ )  መካከል  እርቅ ያስፈልጋል ተባለ።ሰለብሪቲ ኢንሽቲቭ የተባለ ድርጅት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አደረግኩት ባለው ጥናት ድንበር አካባቢ ያለው ህዝብ የሁለቱ ድርጅቶች አመራሮች እርቅ ባለማውረዳቸው ለተለያዩ ችግሮች ተመዳረጉን አስታውቋል።

https://p.dw.com/p/3VIgI
Äthiopien Eritrea l Celebrity Events - Friedensmission
ምስል DW/S. Muchie

እርቅ ዳስ

የኢትዮጵያ እና የኤርትራን ግንኙነት ይበልጥ ለማሻሻል እና  የሁለቱን ህዝቦች ተጠቃሚነት ለማሳደግ በህወኃት እና በኤርትራው ገዥ ድርጅት ህዝባዊ ግንባር ንዲሞክራሲን ፍትህን ( ህግዴፍ )  መካከል  እርቅ ያስፈልጋል ተባለ።ላለፉት 4 አመታት በሁለቱ ሃገራት መካከል እርቅ እንዲወርድ ጥረት ማድረጉን የሚገልጸው ሰለብሪቲ ኢቨንትስ የተባለ ድርጅት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አደረግኩት ባለው ጥናት   ድንበር አካባቢ ያለው ህዝብ የሁለቱ ድርጅቶች አመራሮች እርቅ ባለማውረዳቸው ለተለያዩ ችግሮች ተዳርጓል።ችግሮቹን ለመፍታትም ከ 20 በላይ አባላትን የያዘ "የእርቅ ዳስ" በሚል መርህ እርቅ የሚያፈላልግ ልዑክ ይዞ ወደ አስመራ በቅርቡ እንደሚጓዝ ይፋ አድርጓል።ሰሎሞን ሙጬ ከአዲስ አበባ ዝርዝሩን አዘጋጅቷል።
ሰሎሞን ሙጬ
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ