1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት

ሐሙስ፣ ጳጉሜን 5 2012

ኢትዮጵያ ከሌላው ዓለም በተለየ የራሷ የዘመን ሥሌትና ቀመር ያላት ጥንታዊት ሀገር ናት ። የክረምት ወቅቷ የሚያስከትለው ዝናባማ፣ ቀዝቃዛ የአየር ሁኔታ ተገልጦ ተስፋ ከብርሃናማ የሰማይ ድምቀት፣ ከምድሯ ልምላሜ እና የአደይ አበባ ፍካት ጋር ተደማምሮ በሕዝቧ የአኗኗር ባህል ውስጥ የኖረ፣ ያለና የዳበር ልዩ የአዲስ አመት ክብረ በዓልም አላት።

https://p.dw.com/p/3iHeO
Young Flower Adey Abeba Blumen Äthiopien
ምስል Yohannes Geberegziabeher

«የአዲስ ዓመት አከባበር አንድምታ»

ኢትዮጵያ ከሌላው ዓለም በተለየ የራሷ የዘመን ሥሌትና ቀመር ያላት ጥንታዊት ሀገር ናት ። የክረምቱ ወቅቷ የሚፈጥረው ዝናባማ፣ ብርዳማ አየር ሁኔታ ተገልጦ ተስፋ ከብርሃናማ የሰማይ ድምቀት እና ከምድሯ ልምላሜ እና የአደይ አበባ ፍካት ጋር ተደማምሮ በሕዝቧ የአኗኗር ባህል ውስጥ የኖረ፣ ያለና የዳበር ልዩ የአዲስ አመት ክብረ በዓልም አላት።
ባህላዊ ጨዋታዎች፣ ተስፋ የሰፈፈበትን የጳጉሜን መጨረሻ እና የመስከረም መጀመርያን ታክኮ የሚገለጠው የሀገሬው ሕይወት በግላጭ ይታያል፣ ይደመጣል ፣ ይሸተታል፣ ይቀመሳልም።
ኢትዮጵያዊያን የአዲስ አመት ጅማሮ ወቅታቸውን ሕፃን አዛውንት ፣ ሴት ወንድ ሳይሉ በደስታ፣ በፍቅር ተሰባስበው « እንኳን አደረሰህ አደረሰሽ ፣ መልካም አዲስ አመት ፣ የሰላምና የጤና ዓመት ይሁንልን» እየተባባሉ ያልኖሩትን ነገን በጎ ሆኖ እንዲጠብቃቸው እርስ በእርስ መልካም ምኞታቸውን ይገላለፁበታል። በዛሬው የባህል መሰናዶ ይህንን የኢትዮጵያዊያንን ዘመን የዘለቀና የዳበረ የአዲስ አመት ዋዜማ፣ የክብረ በዓሉን አንድምታና ሕይወት እንዳስሳለን።

ሰለሞን ሙጬ

ሸዋዬ ለገሠ