1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

ረቡዕ፣ ሚያዝያ 6 2013

የቦርዱ ባለስልጣናት ዛሬ ከተቃዋሚ ፖለቲከኞች ጋር ባደረጉት ዉይይት ላይ እንደገለፁት የፌደራልና የክልል መንግስት ፀጥታን እንዲያስከብሩ፣ የምርጫ ጣቢያዎችን፣ የቁሳቁሶች አቅርቦትና ስርጭትን እንዲያመቻቹ ቦርዱ ለሚቀርበዉ ጥያቄ ተገቢዉን መልስ አይሰጡም።

https://p.dw.com/p/3s0gH
Äthiopien | Wahlen in Äthipien, National Election Board of Ethiopia (NEBE) meets political parties
ምስል Yohannes Gebreegiziabher/DW

ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መንግስትን በድጋሚ ወቀሰ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፣ በመጪዉ ግንቦት ለሚደረገዉ ምርጫ  ዝግጅት የፌደራሉንም ሆነ የክልል መንግሥታት ትብብር እንደነፈጉት በድጋሚ አስታወቀ።የቦርዱ ባለስልጣናት ዛሬ ከተቃዋሚ ፖለቲከኞች ጋር ባደረጉት ዉይይት ላይ እንደገለፁት የፌደራልና የክልል መንግስት ፀጥታን እንዲያስከብሩ፣ የምርጫ ጣቢያዎችን፣ የቁሳቁሶች አቅርቦትና ስርጭትን እንዲያመቻቹ ቦርዱ ለሚቀርበዉ ጥያቄ ተገቢዉን መልስ አይሰጡም።ቦርዱ ትብብር በመነፈጉ ምክንያት እስካሁን መክፈት ከሚገባዉ 48 ሺሕ የምርጫ ጣቢያዎች የከፈተዉ 25ሺሕ ብቻ ነዉ።የቦርዱ ባለስልጣናት ከዚሕ ቀደምም ተመሳሳይ ወቀሳ አሰምተዉ ነዉ ነበር።ይሁንና ወቀሳ ከማሰማት ባለፍ መፍትሔ ስለመጠቆሙ አልተዘገበም።

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር 

ነጋሽ መሐመድ

ማንተጋፍቶት ስለሺ