«በሱዳን የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ በክብር ሊወጣ ይገባል» ኢትዮጵያ
ሐሙስ፣ ሰኔ 24 2013ማስታወቂያ
በሱዳን አቢዬ ግዛት የሰፈረው የኢትዮጵያ የሰላም አስከባሪ ኃይል ከተልዕኮው የሚወጣ ከሆነ ተገቢ ፣ ተመጣጣኝ እውቅና እና አክብሮት ተሰጥቶት ሊሆን እንደሚገባ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ይህንን ያለው ሱዳን ሰላም አስከባሪው ኃይል ከግዛቱ ለቅቆ እንዲወጣ ጥያቄ ካቀረበች በኋላ ነው።ኢትዮጵያ በሰላም አስከባሪዎችዋ በተባበሩት መንግሥታት በኩል ከፍተኛ እውቅና አላት ያሉት የሚኒስቴሩ ቃል ዐቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከተባበሩት ማንግሥታት የምስራቅ አፍሪካ የፖለቲካ እና የሰላም ግንባታ ዳይሬክተር ጋር ሰሞኑን በዚሁ ጉዳይ ላይ ውይይት ማድረጋቸውን ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ተናግረዋል።ካለፈው ቅዳሜ ጀምሮ በሳዑዲ አረቢያ በእንግልት ላይ የሚገኙ ዜጎችን ለማምጣት እስካሁን በተደረጉ 35 በረራዎች አሥር ሺህ የሚደርሱ ዜጎች ወደ አገር ውስጥ መግባታቸውንም ቃል ዐቀባዩ በመግለጫቸው ተናግረዋል።ጋዜጣዊ መግለጫውን የተከታተለው የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ሰሎሞን ሙጬ ቀጣዩን ዘገባ ልኮልናል።
ሰሎሞን ሙጬ
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ