1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ ኤኮኖሚ ይዞታ

ሰኞ፣ ሐምሌ 16 2010

ዶቼቬለ ያነጋገራቸው በጉባኤው ላይ ጥናታዊ ጽሁፍ ያቀረቡ አንድ የምጣኔ ሀበት ምሁር ባለፉት ዓመታት ይጠናቀቃሉ ተብለው ይጠበቁ የነበሩ ትላልቅ ፕሮጀክቶች መዘግየት የተለያዩ ተጽእኖዎችን ሊፈጥር እንደሚችል ተናግረዋል። ያን ለማስቀረትም በተቻለ አቅም ሁሉ ፕሮጀክቶቹን ለመጨረስ መሞከር  ተገቢ መሆኑን ገልጸዋል።

https://p.dw.com/p/31xIW
Äthiopien Internationale Konferenz zur äthiopischen Wirtschaft
ምስል DW/G.T. Haile-Giorgis

የኢትዮጵያ ኤኮኖሚ ይዞታ

በኢትዮጵያ ምጣኔ ሀብት ይዞታ ላይ አትኩሮ ካለፈው ሐሙስ እስከ ቅዳሜ የተካሄደው ዓለም አቀፍ ጉባኤ ውጤታማ እንደሆነ አዘጋጆቹ ገለጹ። አዘጋጁ የኢትዮጵያ የኤኮኖሚ ባለሞያዎች ማህበር እንደተናገረው በሦስት ቀናቱ ጉባኤ ላይ በቀረቡት ጥናታዊ ጽሁፎች ደረጃም ይሁን በሌሎች መስፈርቶች ጉባኤው የተሳካ ነበር። ዶቼቬለ ያነጋገራቸው በጉባኤው ላይ ጥናታዊ ጽሁፍ ያቀረቡ አንድ የምጣኔ ሀበት ምሁር ባለፉት ዓመታት ይጠናቀቃሉ ተብለው ይጠበቁ የነበሩ ትላልቅ ፕሮጀክቶች መዘግየት የተለያዩ ተጽእኖዎችን ሊፈጥር እንደሚችል ተናግረዋል። ያን ለማስቀረትም በተቻለ አቅም ሁሉ ፕሮጀክቶቹን ለመጨረስ መሞከር  ተገቢ መሆኑን ገልጸዋል። 
ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ