የኢትዮጵያ መንግስት ወቀሳ
ማክሰኞ፣ ታኅሣሥ 5 2014ማስታወቂያ
ምዕራባዉያን መንግስታት በኢትዮጵያ መንግስት ላይ የሚያደርጉት ግፊትና ጫና አሁንም መቀጠሉን የኢትዮጵያ ዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር አስታወቀ። የሚንስቴሩ ቃል አቀባይ ዲና ሙፍቲ ዛሬ ለጋዜጠኞች እንደነገሩት በመጪዉ ሰኔ ኢትዮጵያ ዉስጥ ሊደረግ የታቀደዉ ዓለም አቀፍ የቴሌኮሙኒኬሽን ስብሰባ ወደ ሌላ ሐገር እንዲዛወር ቅስቀሳ እየተደረገ ነዉ። የአዉሮጳ ሕብረት በኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ጉዳይ ላይ የሚነጋገር ስብሰባ ነገ ጄኔቭ-ሲዊትዘርላድ ዉስጥ እንዲደረግ መጥራቱንም አምባሳደር ዲና አሳዛኝ ብለዉታል። የዓለም ጤና ድርጅት (WHO)ን ጨምሮ የተባበሩት መንግሥታት የተለያዩ ድርጅቶች በአማራና በአፋር ክልሎች በሚገኙ ተቋማት ላይ የደረሰዉን ጥፋት በዝምታ አልፈዉታል በማለት ወቅሰዋልም።
ሰለሞን ሙጬ
ነጋሽ መሐመድ
አዜብ ታደሰ