1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ መንግስት ተደራዳሪዎች ማንነት

ማክሰኞ፣ ሰኔ 21 2014

ምክትል ጠቅላይ ሚንስትርና ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ደመቀ መኮንን የሚመሩት ከሚቴ በአባልነት ካቀፋቸዉ ሰዎች አብዛኞቹ ሕወሓት መራሹ-ኢሕአዴግ ሥልጣን ላይ በነበረበት ወቅት በከፍተኛ የፓርቲና የመንግስት ሥልጣን ላይ የነበሩ ናቸዉ

https://p.dw.com/p/4DNPc
Äthiopien | Demeke Mekonnen Hassen
ምስል Graham Carlow/Creative Commons

የተደራዳሪዉ ኮሚቴ አባላትና ስብጥር

                                                   
የኢትዮጵያ መንግስት ለ19ኝ ወራት ከተዋጋዉ ከሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) ጋር ላቀደዉ ድርድር የሚወክለዉን ኮሚቴ ገዢዉ የብልፅግና ፓርቲ ሰይሟል።ምክትል ጠቅላይ ሚንስትርና ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ደመቀ መኮንን የሚመሩት ከሚቴ በአባልነት ካቀፋቸዉ ሰዎች አብዛኞቹ ሕወሓት መራሹ-ኢሕአዴግ ሥልጣን ላይ በነበረበት ወቅት በከፍተኛ የፓርቲና የመንግስት ሥልጣን ላይ የነበሩ ናቸዉ።የኮሚቴዉ አባል የፍትሕ ሚንስትር  ጌዲዮን ጢሞቲዎስ ትናንት በሰጡት መግለጫ የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት በሰላም እንዲፈታ የፓርቲው የሥራ አስፈፃሚ እና ማዕከላዊ ኮሚቴዎች ወስነዋል፣ ሂደቱም በአፍሪቃ ሕብረት መሪነት ይከናወናል ብለዋል።ሕወሓት ግን ከዚሕ ቀደም ባሰራጨዉ ግልፅ ደብዳቤ የአፍሪቃ ሕብረትን ዋና አደራዳሪ እንደማይቀበል አስታዉቋል።

ሰለሞን ሙጬ 

ነጋሽ መሐመድ

አዜብ ታደሰ