1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮ ኬንያ የተናጠልና የጋራ ፕሮጀክቶች ጠቀሜታ  

ረቡዕ፣ ኅዳር 30 2013

መሪዎቹ ዛሬ በሞያሌ የጠረፍ ከተማ ተገናኝተው አገልገሎት ካስጀመሯቸው ፕሮጀክቶች መካከል የሀዋሳ-ሞያሌ መንገድና የጋራ የፍተሻ ጣቢያ ይገኙባቸዋል።በመንግሥት መገናና ብዙሀን ዘገባ መሠረት የሃዋሳ ሞያሌ መንገድ የሞምባሳ ናይሮቢ አዲስ አበባ ኮሪደር ግንባታ አካል ነው።መንገዱ 6 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር ወጪ ተደርጎበታል።

https://p.dw.com/p/3mUXv
Bildcombo I Abiy Ahmed und  Uhuru Kenyatta

የኢትዮ ኬንያ የተናጠልና የጋራ ፕሮጀክቶች ጠቀሜታ

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ እና የኬንያው ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ሁለቱን አገራት ያስተሳስራሉ ያሏቸውን ፕሮጀክቶች ዛሬ በጋራ መርቀው ከፍተዋል።መሪዎቹ ዛሬ በሞያሌ የጠረፍ ከተማ ተገናኝተው አገልገሎት ካስጀመሯቸው ፕሮጀክቶች መካከል የሀዋሳ-ሞያሌ መንገድና የጋራ የፍተሻ ጣቢያ ይገኙባቸዋል።በመንግሥት መገናና ብዙሀን ዘገባ መሠረት የሃዋሳ ሞያሌ መንገድ የሞምባሳ ናይሮቢ አዲስ አበባ ኮሪደር ግንባታ አካል ነው። 6 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር ወጪ የተደረገበት ይኽው መንገድ በአፍሪቃ ልማት ባንክ የረዥም ጊዜ ብድር ድጋፍ የተሸፈነ ነው።  የሀዋሳው ወኪላችን ሸዋንግዛዉ ወጋየሁ ዛሬ የተመረቁት ፕሮጀክቶች ለኢትዮጵያ እና ለኬንያ የሚሰጡትን ጥቅም በተከታዩ ዘገባው ያስቃኘናል።
ሸዋንግዛው ወጋየሁ
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ