1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮ ኤርትራ የሰላም ስምምነት አንድምታ

ሰኞ፣ መስከረም 21 2011

የኢትዮ ኤርትራ የሰላም ስምምነት እና የሁለቱ ሃገራት የመልካም ንግኙነት ጅማሮ ተጠናክሮ እንዲቀጥል የሚመኙት የሁለቱ ሃገራት ሕዝቦች ብቻ ሳይሆኑ ዓለም አቀፍ ማኅበረሰቡ ጭምር ነው።

https://p.dw.com/p/35p5W
Äthiopien und Eritrea Frieden Logo
ምስል DW/S. Fekade

የሰላም ስምምነቱ ተስፋ ፈንጥቋል

በኤርትራ እና ኢትዮጵያ መካከል ሰላም መውረዱ ለሕዝቦቻቸው ከፈጠረው ደስታ እና ተስፋ በተጨማሪ ለአካባቢው በተለይም ለአፍሪቃ ቀንድ ሃገራት መረጋጋት እና ሰላም መሆን ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንዳለው በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የሚታመነው። ከተጠቀሰው የአፍሪቃ አካባቢ የሚመጡ የስደተኞችን ቁጥር በእጅጉ ይቀንሳል የሚል ተስፋም ያለ በመሆኑ የአውሮጳ ኅብረት ባለስልጣናት የሰላም ስምምነቱ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ እንዳለው ያምናሉ። 

ገበያው ንጉሤv

ሸዋዬ ለገሠ

አዜብ ታደሰ