1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ህወሓት ያሰጋ ይሆን

ረቡዕ፣ ሐምሌ 4 2010

ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ጦርነት ይግጠሙ ወይም ይወዳጁ፤ በፖለቲካ ይሻኮቱ አለያም በምጣኔ ሐብት ቀድሞ የሚነካዉ አንድም ትግራይ ሁለትም አፋር ነዉ። በዚሕም ምክንያት የትግራይ መስተዳድር ከሌሎች አካባቢዎች ቀድሞ ያለዉን ማለቱ ለብዙ ታዛቢዎች «የሚጠበቅ» እና «ተገቢም» ነዉ                           

https://p.dw.com/p/31HtZ
Emblem der Tigray People's Libration Font (TPLF)

TPLF`s position on Ethio-Eritrea agreement - MP3-Stereo

 ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ሠላም ለማዉረድ መስማማታቸዉን የሁለቱ ሐገራት ፖለቲከኞችም፤ የዉጪ መንግስታት፤ ዓለም ዓቀፍ ድርጅቶችም ደግፈዉታል።የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት፤ የአዉሮጳ ሕብረት፤የጀርመን እና የሌሎች የአዉሮጳ መንግስታት በየፊናቸዉ እንዳስታወቁት አዲሱ ግንኙነት ከሁለቱ ሐገራት አልፎ ለአካባቢዉም ሠላም ጠቃሚ ነዉ።ጦርነቱም፤ ሠላሙም ከሌላዉ የኢትዮጵያ ክፍል ቀድሞ የሚነካዉ የትግራይ ሕዝብ እና መስተዳድርም ሠላም ለማስፈን የተጀመረዉን ጥረት እንደሚደግፉ መስተዳድሩ ከትናንት በስቲያ ባወጣዉ መግለጫ አስታዉቋል።የፖለቲካ ተንታኞች ግን ትግራይን የሚያስተዳድረዉ የሕዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ (ሕወሓት) ነባር ባለሥልጣናት ሠላማዊ ጥረቱን እንዳያደናቅፉ ይሰጋሉ።

የመረብ ማዶ፤ለማዶ ሕዝብ በእና ለ ስምምነቱ ደስታ ድጋፉን በአደባባይም፤ በየመገናኛ ዘዴዉም እየገለጠ ነዉ።የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የፍልስፍና መምሕር እና የፖለቲካ አስተያየት ሰጪ ዶክተር ዳኛቸዉ አሰፋ እንደሚሉት ድጋፍ ደስታዉ ከታሰበዉ በላይ ነዉ።
                               
 የትግራይ መስተዳድር ያወጣዉ መግለጫ እንዳለዉ ደግሞ «ወንድማማች» ያላቸዉን የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ሕዝቦች ግንኙነትን ወደነበረበት ለመመለስ መስተዳድሩና ሕዝቡ አብክረዉ ይጥራሉ።ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ጦርነት ይግጠሙ ወይም ይወዳጁ፤ በፖለቲካ ይሻኮቱ አለያም በምጣኔ ሐብት ቀድሞ የሚነካዉ አንድም ትግራይ ሁለትም አፋር ነዉ።
በዚሕም ምክንያት የትግራይ መስተዳድር ከሌሎች አካባቢዎች ቀድሞ ያለዉን ማለቱ ለብዙ ታዛቢዎች «የሚጠበቅ» እና «ተገቢም» ነዉ።የዚያኑ ያክል የሠላም ሥምምነቱ ከዚያዉ ከትግራይ በጣሙን ደግሞ ከሕዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ (ሕወሓት)ነባር መሪዎች እንቅፋት ይገጥመዋል ብለዉ የሚሰጉ ጥቂት አይደሉም።ደራሲ እና የፖለቲካ ተንታኝ አስራት አብረሐም አንዱ ነዉ።
                          
ዶክተር ዳኛቸዉ አሰፋ ግን  የሕወሓት ባለሥልጣናት ሥምምነቱን ያደናቅፉ ይሆናል የሚለዉን ሥጋት አይቀበሉትም።የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀኃፊ አንቶኒዮ ጉተሬሽ የኢትዮጵያ እና የኤርትራን «የሠላምና የወዳጅነት የጋራ መግለጫ»ን፤ ከሁለቱ ሐገሮች፤ ከአፍሪቃም በላይ ለመላዉ ዓለም «በጣም ጠቃሚ ተስፋ» ብለዉታል።የአዉሮጳ ሕብረት ስምምነቱን ከማድንቅ አልፎ፤ የሕብረቱ ቃል አቀባይ ቃል እንደገቡት ገቢራዊነቱን ለማገዝ ይረዳል።የጀርመን ዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር «አስደሳች ዜና» ብሎታል።

Äthiopien 40. Jahrestag TPLF
ምስል DW/T. Weldeyes

ነጋሽ መሐመድ

ኂሩት መለሰ