1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮ-ቤልጂግ እግር ኳስ ቡድን

ረቡዕ፣ ነሐሴ 2 2010

እስካለፈዉ ዕሁድ ድረስ ለአራት ቀን የተካሄደዉ ድግሥት የዝግጅት መሳከር፤ መዝረክረክ እና መተራመስ የተፈጠረበት እንደነበር የበዓሉ ተሳታፊዎች እየተቹ ነዉ።

https://p.dw.com/p/32pgd
Belgien Atomium in Brüssel
ምስል picture-alliance/dpa

(Beri Brussels) Ethio-Belgium Foot ball Team - MP3-Stereo

የዘንድሮዉ የኢትዮጵያዉያን አዉሮጳዉያን የስፖርት እና የባሕል ድግስ ባለፈዉ ሳምንት ሽቱትጋርት ደቡብ ምዕራብ ጀርመን ዉስጥ ተደርጓል። እስካለፈዉ ዕሁድ ድረስ ለአራት ቀን የተካሄደዉ ድግሥት የዝግጅት መሳከር፤ መዝረክረክ እና መተራመስ የተፈጠረበት እንደነበር የበዓሉ ተሳታፊዎች እየተቹ ነዉ። ይሁንና ዘንድሮም እንደከዚሕ ቀደሙ ሁሉ በተለያዩ ሐገራት በሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን የተደራጁ የእግር ኳስ ቡድናት ያደረጉት ግጥሚያ የድግሱ ዋነኛ አካል ነበር። በግጥሚያዉ ከተካፋሉት ቡድናት አንዱ የነበረዉን የኢትዮ-ቤልጂግን የእግር ኳስ ታሪክ የብራስልሱ ወኪላችን ዳግማዊ ሲሳይ ያወጋናል።

ዳግማዊ ሲሳይ

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ