1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮ-ሱዳን ግንኙነትና ምዕራባዉያን መንግስታት

ሰኞ፣ ነሐሴ 24 2013

ከኢትጵያ ዘግየት ብላ የፖለቲካ ሽግግር የጀመረችዉ ሱዳን ግን ከኢትዮጵያ ጋር እየተወዛገበችም፣ በዉስጧ የተሻለ ሠላምና መረጋጋት ማስፈን ችላለች።ምዕራባዉያን መንግሥታትም ኢትዮጵያን የማግለልና የመቅጣታቸዉን ያክል ለሱዳን ከፍተኛ ድጋፍና ርዳታ እየሰጡዋት ነዉ

https://p.dw.com/p/3zhPN
Yesuf Yassien
ምስል privat

የኢትዮጵያና ሱዳን ግንኙነት፣የምዕራቡ ዓለም አቋም

ኢትዮጵያ በርስበርስ ጦርነትና ግጭት፣ ሱዳንና ግብፅን ከመሳሰሉ ሐገራት ጋር ደግሞ በግድብና በድንበር ግዛት ይገባኛል ሰበብ የገጠመችዉ ዉዝግብ እየተካረረ ነዉ።ምዕራቡ ዓለምም ለወትሮዉ «ጥብቅ ወዳጅ» ይላት የነበረችዉን ኢትዮጵያን እያገለ፣ በማዕቀብም እየቀጣ ነዉ።ከኢትጵያ ዘግየት ብላ የፖለቲካ ሽግግር የጀመረችዉ ሱዳን ግን ከኢትዮጵያ ጋር እየተወዛገበችም፣ በዉስጧ የተሻለ ሠላምና መረጋጋት ማስፈን ችላለች።ምዕራባዉያን መንግሥታትም ኢትዮጵያን የማግለልና የመቅጣታቸዉን ያክል ለሱዳን ከፍተኛ ድጋፍና ርዳታ እየሰጡዋት ነዉ።የሁለቱ ተጎራባች ሐገራት ፖለቲካዊ ዕዉነት፣ ቁርቁስና የምዕራቡ ዓለም አቋምን በተመለከተ ከደራሲና ከፖለቲካ ተንታኝ ዩስፍ ያሲንን ጋር ያደረግነዉን አጭር ቃለ መጠይቅ አድምጡ።

ነጋሽ መሐመድ