1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮ ሱዳን የድንበር ይገባኛል ውዝግብ እና ያገረሸው ስጋት

ቅዳሜ፣ ግንቦት 20 2014

የኢትዮጵያ እና የሱዳን የድንበር ውዝግብ በሁለቱ አገሮች በሠላም ካልተቋጬ ቀጣናዊ እና አህጉራዊ ድርጅቶች ሊገቡበት ይገባል ሲሉ የፖለቲካ ተንተኞች አሳሰቡ። የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከሰሞኑ ሱዳን በወረራ የያዘችው የኢትዮጵያ ድንበር በምንም መመዘኛ ይመለሳል ብሏል።

https://p.dw.com/p/4BzHW
Karte Sudan Äthiopien EN

መፍትሄ ያልተበጀለት የኢትዮ ሱዳን የድንበር ውዝግብ እንደ አዲስ አገርሽቷል

የኢትዮጵያ እና የሱዳን የድንበር ውዝግብ በሁለቱ አገሮች በሠላም ካልተቋጬ ቀጣናዊ እና አህጉራዊ ድርጅቶች ሊገቡበት ይገባል ሲሉ የፖለቲካ ተንተኞች አሳሰቡ።
የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከሰሞኑ ሱዳን በወረራ የያዘችው የኢትዮጵያ ድንበር በምንም መመዘኛ ይመለሳል ብሏል።
ይህ የመንግሥት ውሳኔ ሁለቱን አገራት ኃይል ወደ መጠቀም ሊገፋቸው ይችላል ያሉ የፖለቲካ ተንታኝ የሁለቱ አገሮች ሕዝቦች ያላቸውን መልካም የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት መሠረት አድርገው ችግሩን በሠላም የመፍታቱን አማራጭ ሊመርጡ እንደሚገባ ጠቁመዋል።
የኢትዮጵያ መንግሥት ሱዳን ሉዓላዊ ግዛቴን በኃይል ከመያዝ አልፋ በሽብርተኝነት ለተፈረጀው ሕወሓት ከለላ በመስጠት ከመውጋት የማይተናነስ ችግር ፈጥራብኛለች ብሏል።

ሰለሞን ሙጬ

ታምራት ዲንሳ