1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮ ምህዳር ዋና አዘጋጅ መፈታት

ሰኞ፣ ሰኔ 26 2009

የሳምንታዊው ኢትዮ ምህዳር ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ጌታቸው ወርቁ ከእስር ተፈታ። ጋዜጠኛ ጌታቸው የታሰረው በአዲስ አበባ በኦርቶዶክስ ቤ/ክርስትያን መንበረ ፓትርያርክ ቅድስት ማርያም ገዳም ውስጥ አለ ስለተባለ ችግር በማስረጃ አስደግፎ ከአንድ ዓመት ከአምስት ወር በፊት ዘገባ በማቅረቡ ባለፈው ህዳር በስም ማጥፋት ወንጀል ክስ ከተመሰረተበት በኋላ ነው።

https://p.dw.com/p/2fqdH
Waage der Göttin Justitia
ምስል dpa

Ber. AA(Ethio Mehdar Journalist Getachew Worku freigelassen) - MP3-Stereo

የአንድ ዓመት እስራት እና የገንዘብ ቅጣት ክፍያ ተፈርዶበት የነበረው እና ጋዜጣውም የተዘጋበት  ጋዜጠኛ ጌታቸው ወርቁ፣ የአዲስ አበባ ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገብረእግዚአብሄር እንደገለጸልን፣ ትናንት በአመክሮ ተፈቷል፣ የመዘጋት እጣ ያጋጠመውን «ኢትዮ ምህዳር»ን መልሶ የመጀመር ፍላጎትም አለው። የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ጋዜጠኛ ጌታቸው ወርቁን አነጋግሮታል።  

ዮሐንስ ገብረእግዚአብሄር

አርያም ተክሌ

ሂሩት መለሰ