1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢራን ዩናይትድስ ስቴትስ ፍጥጫ

ረቡዕ፣ ታኅሣሥ 29 2012

የኢራን እና የዩናይትድ ስቴትስ ፍጥጫ አይሎ ወደ ግጭት እያመራ ነው። ኢራን የአብዮታዊ ዘቧ የመሪው ጄኔራል ቃሲም ሶሌይማኒን ግድያ ለመበቀል በሚል ዛሬ ማለዳ ላይ ጎረቤት ሀገር ኢራቅ ውስጥ የሚገኙ የዩናይትድ ስቴትስ የጦር ሰፈሮች ላይ 22 የባለስቲክ ሚሳይሎችን አስወንጭፋለች።

https://p.dw.com/p/3Vu7U
Irak Irans Vergeltungsschlag kommt mit Vorwarnung
ምስል Reuters/Handout Iran Press

ፍጥጫው ወዴት እያመራ ነው?

የኢራን እና የዩናይትድ ስቴትስ ፍጥጫ አይሎ ወደ ግጭት እያመራ ነው። ኢራን የአብዮታዊ ዘቧ የመሪው ጄኔራል ቃሲም ሶሌይማኒን ግድያ ለመበቀል በሚል ዛሬ ማለዳ ላይ ጎረቤት ሀገር ኢራቅ ውስጥ የሚገኙ የዩናይትድ ስቴትስ የጦር ሰፈሮች ላይ 22 የባለስቲክ ሚሳይሎችን አስወንጭፋለች። የኢራን ፕሬዚደንት ሐሰን ሮሐኒ የሚሳይል ጥቃቱ ጄኔራሉ ላይ በዩናይትድ ስቴትስ ለተፈጸመው ግድያ መልስ ነው ብለዋል። አሜሪካንን በተመለከተም «አናፈገፍግም» ሲሉ ተደምጠዋል። ውጥረቱ በአሁኑ ወቅት በመካከለኛው ምሥራቅ ምን ይመስላል? የመካከለኛው ምሥራቅ ዋና ዋና የመገናኛ አውታሮች ምን አሉ? ኢራቅ ውስጥ የሚገኘው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ተልዕኮ ኢራን ሁለት የዩናይትድ ስቴትስ የኢራቅ ይዞታዎች ላይ የሚሳይል ጥቃት ካደረሰች በኋላ በሰጠው መግለጫ ኢራን፦ «ዋጋ የሚያስከፍላትን» ነገር መሥራት አይገባትም ብሏል። የተለያዩ የአውሮጳ ሃገራት በዩናይትድ ስቴትስ እና ኢራን ፍጥጫ የየራሳቸውን አቋም እያንጸባረቁ ነው። ብሪታንያ የኢራንን ድርጊት አውግዛለች፤ በተመሳሳይ የኢራንን ድርጊት ያወገዘችው ጀርመን በሃገራቱ መካከል ውይይት ይደረግ እያለች ነው። ፈረንሳይም ውጥረቱን ለማርገብ ከሁሉም ወገን እንደምትሠራ አስታዉቃለች። የኢራን ዩናይትድ ስቴትስ ፍጥጫን በተመለከተ የዓረብ ሃገራቱ አቋም ምን ይመስላል?

ለጥያቄዎቹ መልሶቹን ከድምፅ ማእቀፉ ያድምጡ።

ነቢዩ ሲራክ 
ማንተጋፍቶት ስለሺ
አዜብ ታደሰ