1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ፖለቲካየመካከለኛው ምሥራቅ

የኢራን አዲሱ ፕሬዝደንት

ሐሙስ፣ ሐምሌ 29 2013

አዲሱ የኢራን ተመራጭ ፕሬዝደንት ኢብራሂም ራይሲ ዛሬ ከሀገሪቱ ፓርላማ ፊት ቀርበው ስምንተኛው የመሪ በመሆን የመንግሥቱን ሥልጣን ተረከቡ። ሃይማኖታዊው የኢራን መሪ አሊ ኻሚኒ ፕሬዝደንት ኢብራሂም ራይሲን ሥልጣን ቢያጸድቁም አዲሱ ፕሬዝዳንት በቴህራንና በዋሽንግተን መካከል ያለውን ውጥረት ያረግቡት ይሆን ይብዙዎች ጥያቄ ነው።

https://p.dw.com/p/3ybAR
Teheran, Iran | Ebrahim Raisi | neu gewählter Präsident
ምስል Vahid Salemi/AP Photo/picture alliance

የቴህራን ዋሽንግተንን ግንኙነት ያሻሽሉ ይሆን?

አዲሱ የኢራን ተመራጭ ፕሬዝደንት ኢብራሂም ራይሲ ዛሬ ከሀገሪቱ ፓርላማ ፊት ቀርበው ስምንተኛው የመሪ በመሆን የመንግሥቱን ሥልጣን ተረከቡ። ባለፈው ማክሰኞ በተካሄደ ሌላ ስነስርዓት ራይሲ የሀገሪቱን ከፍተኛ የሃይማኖት መሪ የአያቶላ አሊ ኻሚኒን ቡራኬም ተቀብለዋል። አያቶላ ኻሚኒ የፕሬዝደንቱን ሹመት ሲያጸድቁም ምጡቁን የማይደክመውን እና ከፍተኛ ልምድ ያለውን ራይሲን የኢራን ፕሬዝደንት እንዲሆን ሹመቱን አጽድቄያለሁ ማለታቸውን ገበያው ንጉሤ ከብራስልስ በላከው ዘገባ  ጠቅሷል። ሃይማኖታዊው የኢራን መሪ ይኽን ቢሉም አዲሱ ፕሬዝዳንት በቴህራንና በዋሽንግተን መካከል ያለውን ውጥረት ያረግቡት ይሆን ይብዙዎች ጥያቄ ነው። ዝርዝሩን እነሆ።

ገበያው ንጉሤ

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ