1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የታሪክ ትምሕርቶችና የቅኝ ግዛት ታሪክ

ቅዳሜ፣ መስከረም 30 2013

አንዳንድ የአፍሪቃ የትምሕርት መጻህፍት አሁንም የቅኝ ገዢዎችን አመለካከቶች እንዳካተቱ ነው።በርካታ አፍሪቃውያን ፣የአፍሪቃ ታሪክ ከራስዋ ከአፍሪቃ እይታ አኳያ ሊጻፍ ሊተረክ ይገባል ሲሉ ድምጻቸውን እያሰሙ ነው።በሌላ በኩል በጀርመን ፣የሃገሪቱ የቅኝ ግዛት ታሪክ በስርዓተ ትምሕርቶች ውስጥ እምብዛም ቦታ አለማግኘታቸው ጥያቄ አስነስቷል።

https://p.dw.com/p/3jiQV
BG 400 Jahre Sklavenhandel Westafrika
ምስል picture-alliance/akg-images

የአፍሪቃና የጀርመን የታሪክ ትምሕርቶችና የቅኝ ግዛት ታሪክ

አንዳንድ የአፍሪቃ የትምሕርት መጻህፍት አሁንም የቅኝ ገዢዎችን አመለካከቶች እንዳካተቱ ነው።በርካታ አፍሪቃውያን ፣የአፍሪቃ ታሪክ ከራስዋ ከአፍሪቃ እይታ አኳያ ሊጻፍ ሊተረክ ይገባል ሲሉ ድምጻቸውን እያሰሙ ነው።በሌላ በኩል በጀርመን ፣የሃገሪቱ የቅኝ ግዛት ታሪክ በስርዓተ ትምሕርቶች ውስጥ እምብዛም ቦታ አለማግኘታቸው ጥያቄ አስነስቷል።

ከአፍሪቃ በርዝመት ሦስተኛው ወንዝ ኒጀር የተባለው ወንዝ ነው።ከደቡባዊ ጊኒ ከፍተኛ ቦታዎች ተነስቶ አትላንቲክ ውቅያኖስ የሚገባው የኒጀርን ወንዝ ማን አገኘው ሲባል ፣መልሱ በናይጀሪያ የታሪክ መጸሐፍ ውስጥ ይገኛል። ስኮትላንዳዊው ሙንጎ ፓርክ በ1796 ዓም  4200 ኪሜትር ርዝመት ያለውን ይህን ወንዝ ማግኘቱ ሰፍሯል።ናይጀሪያዊቷ ፌዝ ኦዶሌ ይህን ድሮ ተምረውታል።የአሁንዋ የታሪክ ምሁር ኦዴሌ ከድሮ የናይጀሪያ ጥንታዊ ታሪክ ለህጻናት የሚሆኑ ታሪኮችን ይሰበስባሉ።የኒጀር ወንዝ በስኮትላንዳዊው ፓርክ ነው የታወቀው መባሉ ሁሌም የሚገርማቸው ጉዳይ ነው።
« ማነው ኒጀር ወንዝን ያገነው ተብሎ ሲጠየቅ።ሙንጎ ፓርክ ነው ያገኘው ነው መልሱ።ከዚያም መገረም ትጀምራለህ።ሙንጎ ፓርክ ወደዚህ ከምምጣቱ በፊት ወenzu አeln,በረም ማለት ነው?ሰዎች ወደ ወንዙ አይሄዱም ነበር?አሳስ አያጠምዱም ነበር?ታዲያ ለምንድን ነው ናይጀሪያውያን ፣ናይጀሪያውያን ህጻናትን ሙንጎ ፓርክ i።ኒጀር ወንዝን አገኘ ተብለው የሚማሩት።»
የዚህ ዘገባ ጸሀፊ የዶቼቬለዋ ሲሊያ ፍሮህሊሽ ሌሎች ምሳሌዎችንም ታነሳለች ።በአንድ የጋና የማኅበራዊ ሳይንስ መጸሐፍ ለተማሪዎች አንድ ጥያቄ ቀርቧል።ጥያቄው የቅኝ ግዛት አዎንታዊ ተጽእኖዎች ምንድናቸው የሚል ሲሆን አራት መልሶች ተደርድረዋል፤ሀ፦ ትምህርት ቤቶች መከፈታቸው ፣ለ፦እንግሊዘኛ መታወቁ ሐ፦የውጭ እቃዎች ፍላጎት መ፦የከተማ እድገት የሚሉ። 
በአፍሪቃ ቅኝ አገዛዝ ካበቃ ከ60 ዓመት በኋላም በበርካታ የአፍሪቃ ሃገራት፣ ያለፈው አስተሳሰብ አሁንም የታሪክ ትምሕርቶች ላይ ተጽእኖ እያሳደረ መሆኑን የቦትስዋናዋ ደራሲ ሲያንዳ ሞሁቲዋ ያስረዳሉ።
እርሳቸው እንደሚሉት ትኩረቱ ሁሉ በጎርጎሮሳዊው 1966 የተገኘው ነጻነት ላይ ብቻ እንጂ ሌላው ጉዳይ አይደለም ።ሞሁትሲዋ እንደሚሉት እንዲያውም አስተማሪዎች ይህን ወቅት ፍጹም ማንሳት የሚፈልጉ አይመስልም ።ስለ19ነኛው ክፍለ ዘመን የአፍሪቃ ነገድ የተማሩት በጀርመን ነገሥታትና በብሪታንያውያን እይታ በተጻፉ መጸሐፍት ነው።እናም እንደርሳቸው ችግሩ ሥር የሰደደ ነው።
«በመጀመሪያ ደረጃ መደበኛ ትምሕርት በአስራ ስምንተኛው ዘመን አጋማሽ በብሪታኒያ ነው የተፈለሰፈው ። ይህም ከብሪታንያ ቅኝ አገዛዝ መስፋፋት ጋር ተገጣጠመ።ህጻናትን ደረጃውን በጠበቀ ሥርዓተ ትምሕርት ለማስተማር ሲዘጋጁ ሌሎች ሃገሮችንም እንዴት ቅኝ እንደሚገዙ እየተማሩ ነበር።ይህም፣ እነዚህ ነገሮች እርስ በርሳቸው እንዲደጋገፉ አድርገዋል።ማለትም ጥቁርነትን ፣ኔግሮነትን፣ ህንዶችንና ሌሎችንም የተመለከቱ ሃሳቦችን ለመፍጠር ረዳቸው።ይህን ያደረጉትም ሰዎችን በባርነት ማስተዳደር ጥሩ ሃሳብ መሆኑን ለብሪታንያ ሕዝብ ማሳመን ስለነበረባቸው ነው።»ይህን እንዲሳካም ብዙ ርብርብ ተደርጓል።
«የነጮች የበላይነትን ትርክት ለመፍጠር እንዲረዷቸው በርካታ ታዋቂ ሰዎችን ቀጠሩ። እነዚህ ኔግሮዎች እነዚህ ደግሞ ጥቁሮች ብለን እናስተምራቸው አሉ።እነዚህ ያንሳሉ ሌሎቹ ይበልጣሉ እያሉ ደረጃ አወጡ።እናም  ይህ አስተሳሰብ እና ትምሕርት ቅኝ ወደ ተገዙ ሃገራት ተይዞ ሲመጣ ምን እንደሚሆን አስቡ።»
ናይጀሪያዊትዋ የታሪክ ምሁር ኦዴሌም ችግሩ ስር የሰደደ መሆኑን ነው የሚናገሩት።የአንድ ሃገር ታሪክ ፣ማንነትን ለማወቅ ወሳኝ ነው የሚሉት ኦዴሌ የተሳሳተ ምስል እስከቀረበልን ድረስ ያለፈው ኢፍትሃዊነት መቀጠሉ አይቀርም ይላሉ።ኦዴሌ እንደሚሉት በ1990ዎቹ ፣የታሪክ ትምሕርት በናይጀሪያ ስርዓተ ትምሕርቱ ውስጥ አልነበረም።በአሁኑ ጊዜም የናይጀሪያን የቅኝ ግዛት ታሪክ የማያውቁ ብዙ ናይጀርያውያን እንዳሉ ነው የሚናገሩት።እናም በርሳቸው አስተያየት መንግሥት ህዙቡ የቀደመውን ታሪኩን እንዲያውቅ አይፈለግም ፤ይህንንም የሚያደርግበት ምክንያት አለው ይላሉ። 
«ታሪካችንን ካወቅን ከእንቅልፋችን እንነቃለን።መንግሥታችን ደግሞ ህዝቡ እንዲነቃ አይፈልግም።እኛ ድሀ እንደሆን፣ኃይል እንደሌለን፣ እየተሰማን እንድንኖር ነው የሚፈለገው።ምክንያቱም ህዝቡ ካወቀ ተቃውሞ ይቀሰቅሳል።ህዝቡ ስለ ቀድሞ ታሪኩ ባያውቅ ነው እነርሱ የሚፈልጉት።በቅኝ ግዛት ዘመን አመጽ እንደነበረ ህዝቡ ካላወቀ፣ስለ ናይጀሪያ አመሰራረት ካላወቀ መንግሥትን ሊጠይቅ አይችልም።»
ያም ሆኖ በታሪክ ትምሕርት ውስጥ የአፍሪቃውያንን እይታ ለማካተት ጥረቶች መደረጋቸው አልቀረም።የኬንያ መንግሥት፣ በጎርጎሮሳዊው 2019 የተመ የትምሕርት የሳይንስ የባህል ድርጅት ዩኔስኮ ያወጣው ለዚህ ዓላማ የታሰበ ምክረ ሃሳብን ማጽደቅ እንደሚፈልግ አስታውቋል።የዩኔስኮው መርሃ ግብር ዓላማ የአፍሪቃን ታሪክ በአግባቡ ማደራጀት ነው።ይኽውም የአፍሪቃ ታሪክ ከባርያ ንግድና ከቅኝ ግዛት ከመነጩ ዘረኛ አስተሳሰቦች የጸዳ የአፍሪቃን እይታ የሚያካትትና የሚያራምድ እንዲሆን ማድረግ ነው።ከ1964 አንስቶ 230 የታሪክ ምሁራንና ሌሎች ባለሞያዎች ይህን ሲያከናውኑ ቆይተዋል።የደቡብ አፍሪቃ የትምሕርት ሚኒስትር በጎርጎሮሳዊው 2019 መጨረሻ የደቡብ አፍሪቃና፣ የአፍሪቃ ታሪክ ከእስከዛሬው በተለይ ለሦስት ተጨማሪ ዓመታት እንዲሰጥ ጥሪ አቅርበው አዲስ የታሪክ ስርዓተ ትምሕርት ገቢራዊ እንደሚሆን ተናግረዋል።በቦትስዋናም ለውጦች አሉ።ደራሲ ሞሁትሲዋ እንደሚሉት በቦትስዋና ለብዙ ዓመታት በአስተማሪነት ያገለግሉ የነበሩት ነጮች ነበሩ። አሁን ግን ያ ተቀይሮ ቦትስዋናውያን ናቸው የሚያስተምሩት።
ጀርመናውያን ከጎሮጎሮሳዊው 1918 በፊት ለ30 ዓመታት በአፍሪቃና በምዕራባዊ ፓስፊክ ቅኝ ግዛቶችን ያስተዳድሩ ነበር።ይህ ታሪክ ግን በበርካታ ጀርመናውያን ዘንድ አይታወቅም ይላል የዶቼቬለው ፔተር ሄለ።የዚህ ምክንያቱ የጀርመን ተማሪዎች ስለ ሃገራቸው የቅኝ ግዛት ታሪክ ቢማምሩም፣ጥቂት መሆኑ አለያም ምንም አለመማራቸው ነው። የጀርመን ተማሪዎች ቅኝ ገዥዎችን የታገለው ናሚብያዊው ሄንድሪክ ቪትቦይ ማነው ተብለው ቢጠየቁ መልስ የላቸውም። ጀርመን ቅኝ በገዛችው በምዕራብ አፍሪቃ ስለተካሄደው የነጻነት ትግል ሁሉም ማለት ይቻላል አያውቅም።በናሚቢያዎቹ በሄሬሮና በናማ ጎሳዎች ላይ የተፈጸመው የዘር ማጥፋት ወንጀልን ብዙዎች አያውቁም።የዚህም ምክንያቱ የጀርመን የ30 ዓመታት የአፍሪቃና የምዕራብ ፓስፊክ የቅኝ ግዛት ታሪክ በጀርመን ስርዓተ ትምሕርትና በመማሪያ መጻህፍት ምንም ቦታ አለማግኘቱ ነው።የጀርመን 16ቱ ፌደራል ክፍለ ሃገራት የራሳቸውን ስርዓተ ትምሕርት አላቸው።በአንዳንድ ግዛቶች ርዕሱ በትምሕርት ቤቶች አይነሳም።በአንዳንዶቹ ደግሞ በጣም በትንሹ ይነካ ይሆናል ትላለች አቢጋኤል ፉጋህ።የኮሎኝ ከተማ ነዋሪ የሆነችው የ26 ዓመቷ አቢጋል ፉጋህ ይህ እንዲለወጥ የሃሳቡን ደጋፊዎች ፊርማ  እያሰባሰበች ነው
«አሁን በትምሕርት ቤቶች የሚሰጠው ትምሕርት በቂ አይደለም።ስለዚህ የስርዓተ ትምህርትና የመጻህፍት ክለሳ መካሄድ አለበት።ጥቁር ልጆች በእድሜያቸው ዘረኝነት እንደሚፈጸምባቸው ሁሉ ነጮች ልጆች ደግሞ ስለዚህ ለማወቅ ብቁ ናቸው።» 
ወላጆችዋ ከጋና የመጡት ፉጋ እንደምትለው በትምሕርት ቤትዋ አስተማሪዎች ጉዳዩን ብዙም አያተኩሩበትም። አሁን ያለውን ዘረኝነት መረደትና መቋቋም የሚችሉት የቅኝ ግዛትን ታሪክ የሚያውቁት ብቻ ናቸው ነው የምትለው ፉጋ እስካሁን 95 ሺህ የሚደርስ ሰው ፊርማ አሰባስባለች።የቅኝ ግዛት ታሪክ የስርዓተ ትምሕርቱ አካል ነው ሲሉ የጀመረችውን ዘመቻ መምህራን እንደሚያጣጥሉባት የምትናገረው ፉጋ ችግሩ ትምሕርቱ ግዴታ አለመሆኑ ነው ትላለች።
በሆሎኮስት 6 ሚሊዮን አይሁድች መጨፍጨፋቸው፣ሁለተኛው የዓለም ጦርነት ቀዝቃዛው ጦርነት  የምሥርቅና ምዕራብ ጀርመን ክፍፍል እነዚህ ሁሉ በጀርመን የታሪክ ትምሕርት ትልቅ ቦታ አላቸው።ከዚያ የተረፈው ግን በተማሪውና በአስተማሪዎች ፍላጎት የሚወሰን ነው። ኢምከ ሽታልማን በሰሜን ጀርመንዋ በሀምቡርግ ከተማ የሁለተኛ ደረጃ ትምሕርት ቤት መምህርት ናቸው።ርሳቸው በሚያስተምሩበት በፋርምሰን ትምህርት ቤት የጀርመን የቅኝ ግዛት ታሪክ ትምህርት ይሰጣል።
«በትምህርት ቤታችን ላለፉት 15 ዓመታት የጀርመን የቅኝ ግዛት ታሪክ ላይ አትኩረን ሰርተናል። ትምሕርቱ ወቅታዊ ዓለም አቀፍ ጉዳዮችን ለመረዳት ይጠቅማል።»
ሽታልማን የሚያስተምሩበት የፋርምሰን ሁለተኛ ደረጃ ትምሕርት ቤትቻንጎምቤ ከተባለው ታንዛንያ ዳሬሰላም ከሚገኝ ትምሕርት ቤት ጋር ከ2018 ዓም ጀምሮ የልምድ ልውውጥ ያካሂዳል።የቀድሞዋ ቅኝ ገዥ ጀርመን ተማሪዎች፣ ከቀድሞዋ የጀርመን የምሥራቅ አፍሪቃ ቅን ግዛት ተማሪዎች ጋር በኢንተርኔት ሃሳብ በመለዋወጥ ጀምረው በኃላም ታንዛኒያዎቹ ተማሪዎች ሃምቡርግ መጥተውም ልምዳቸውን አካፍለዋል።አቢጋል ፉጋህ ይህን መሰሉን መድረክ ሁሉም ትምሕርት ቤት ሊያዘጋጅ እንደማይችል ትረዳለች።ሆኖም የጀርመን ተማሪዎች የቀድሞውን የቅኝ ግዛት ታሪክ፣ የወረሱትንና የራሳቸውን የዘረኝነት ታሪክ እንዲያውቁ እድሉ እንዲሰጣቸው ነው የምትፈልገው።ለዚህ ጉዳይ የበኩልዋን  አስተዋጽኦ ማድረግም ትፈልጋለች።በአሁኑ ጊዜም ፣ወደፊት በትምሕርት ቤቶች የጸረ ዘረኝነት ትምሕርት መስጠት የሚያስችላት ስልጠና እየወሰደች ነው።

Abigail Fugah
ምስል Privat
Namibia Geschichte Deutsch-Südwestafrika Gefangene Hereros
ምስል ullstein bild
Sudan Buch ' Africa - Romanticised German view of the 'Scramble for Africa'
ምስል picture-alliance/CPA Media Co. Ltd
Kongokonferenz Berlin
ምስል picture-alliance/akg-images

ኂሩት መለሰ

ልደት አበበ