1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአፍሪቃ ኅብረት አስቸኳይ ጉባኤ በሱዳን እና ሊቢያ ወቅታዊ ጉዳይ

ቅዳሜ፣ ሚያዝያ 19 2011

በሱዳን ወቅታዊ ኹኔታ ላይ እና በሊቢያ እየካሄደ ባለው ጦርነት ለመምከር የተጠራው የአፍሪቃ ኅብረት አስቸኳይ መሪዎች ጉባኤ ማክሰኞ፤ ሚያዝያ 15 ቀን፣ 2011 ዓ.ም ግብጽ ካይሮ ከተማ ውስጥ ተካሂዷል። ግብጽ የወቅቱ የአፍሪቃ ኅብረት ስትሆን፤ ስብሰባውን የጠሩትም ፕሬዚደንቷ አብደል ፋታኅ ኧል ሲሲ ናቸው።

https://p.dw.com/p/3HZBy
Ägypten Kairo - Gipfeltreffen
ምስል Reuters/The Egyptian Presidency

በሱዳን እና ሊቢያ ወቅታዊ ጉዳይ

በሱዳን ወቅታዊ ኹኔታ ላይ እና በሊቢያ እየካሄደ ባለው ጦርነት ለመምከር የተጠራው የአፍሪቃ ኅብረት አስቸኳይ መሪዎች ጉባኤ ማክሰኞ፤ ሚያዝያ 15 ቀን፣ 2011 ዓ.ም ግብጽ ካይሮ ከተማ ውስጥ ተካሂዷል። ግብጽ የወቅቱ የአፍሪቃ ኅብረት ስትሆን፤ ስብሰባውን የጠሩትም ፕሬዚደንቷ አብደል ፋታኅ ኧል ሲሲ ናቸው። መሪዎቹ በሱዳን  የቀድሞው ፕሬዚደን አልበሽርን የተኩት የሱዳን  ወታደራዊ ባለሥልጣናት የመንግሥቱን ሥልጣን በተወሰነ  ጊዜ ለሲቪል አስተዳደር እንዲያስረክቡ አስጠቅቀዋል። የአፍሪቃ ኅብረት አስቸኳይ የመሪዎች ጉባኤ ሲጠናቀቅ በሊቢያም የፖለቲካ ውይይት እንዲጀመር በማሳሰብ ነበር።

አስቸኳይ ስብሰባው የሱዳኑ የረዥም ጊዜ ፕሬዚደንት ዖማር ሐሠን ኧል በሽር በሀገሪቱ ወታደራዊ ኃይል ከሥልጣናቸው ከተነሱ በኋላ በሱዳን ስለቀጠለው ተቃውሞ መክሯል። በሊቢያ ጄነራል ካሊፋ ሐፍታር ወደ ትሪፖሊ በመገስገስ የጀመሩት የጥቃት ዘመቻ የፈጠረውን «ወቅታዊ ቀውስ ለማብረድ» በሚልም ውይይት ተካሂዷል። 

የትኩረት በአፍሪቃ ዐበይት ርእሰ ጉዳዮች ናቸው።

ገበያው ንጉሤ

ማንተጋፍቶት ስለሺ