1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአፍሪቃ ቀንድ የፈረንሳይ የኢትዮጵያ ማሕበር

ሐሙስ፣ ሰኔ 14 2010

የአፍሪቃ ቀንድ የፈረንሳይ የኢትዮጵያ ማሕበር በሚል ፈረንሳይ ውስጥ የኢትዮጵያ ወዳጆችን ያሰባሰበ ማሕበር ይገኛል። የማሕበሩ መሥራች በልጅነቱ ከተወለደባት ሀገር ኢትዮጵያ ወደ አውሮጳ ፈረንሳይ የመጣ የድሬ ልጅ ነው።

https://p.dw.com/p/302or
Kulturelle Vereinigung zwischen Äthiopien und Frankreich
ምስል DW/H.Tiruneh

ባህል እና ታሪክን ለፈረንሳውያን ማሳወቅ

 
የአፍሪቃ ቀንድ የፈረንሳይ የኢትዮጵያ ማሕበር በሚል ፈረንሳይ ውስጥ የኢትዮጵያ ወዳጆችን ያሰባሰበ ማሕበር ይገኛል። የማሕበሩ መሥራች በልጅነቱ ከተወለደባት ሀገር ኢትዮጵያ ወደ አውሮጳ ፈረንሳይ የመጣ የድሬ ልጅ ነው። ማሕበሩ ዋና ሥራው የኢትዮጵያን ባህል እና ታሪክ ለፈረንሳውያን ማሳወቅ ሲሆን ኢትዮጵያ ውስጥ ደግሞ የተለያዩ የልማት ተግባራትን ያከናውናል። 10 ዓመት ባስቆጠረው በዚህ ማሕበር አማካኝነት የፈረንሳይዋ ሊዮ ከተማ ከአፍሪቃ መዲናዋ ከአዲስ አበባ ጋር፤ የፈረንሳይዋ ቪለርቫን ከተማ ደግሞ ከድሬደዋ የትብብር ትስስር ፈጥረዋል። የባህል መድረክ መሰናዶ የአፍሪቃ ቀንድ የፈረንሳይ የኢትዮጵያ ማሕበር የኢትዮጵያን ባህል እና ታሪክ በማስተዋወቅ ረገድ ያከናወነውን ያስቃኛል።


ሃይማኖት ጥሩነህ

አዜብ ታደሰ