1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአፍሪቃ ቀንድ መሪዎች ጉብኝትና ውይይት

ማክሰኞ፣ የካቲት 26 2011

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከሳምንቱ መጨረሻ ቀናት አንስቶ ከሰሞኑ ከአፍሪቃ ቀንድ ሃገራት መሪዎች ጋር ያላሰለሰ ውይይት ብሎም በሃገራቱ ጉብኝት ሲያደርጉ ሰንብተዋል።

https://p.dw.com/p/3ETT2
Addis Abeba
ምስል Haile

«የሃገራቱን መቀራረብ እና ትስስር ለማጠናከር ነው»

የኬንያውን ፕሬዝደንት ተቀብለው ባስተናገዱ ማግሥት ወደ አስመራ ኤርትራ፣ ከዚያም የኤርትራውን ፕሬዝደንት አክለው ወደ ደቡብ ሱዳን በመጓዝ ከመሪዎቹ ጋር በአካባቢው ሰላም፤ የኤኮኖሚ ትስስር እና የመሠረተ ልማት ጉዳዮች ጋር መምከራቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ይፋ ባደረገው መረጃዎች አመልክቷል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ዛሬ ደግሞ የሶማሊያውን ፕሬዝደንት መሐመድ አብዱላሂ መሐመድን አዲስ አበባ ላይ ተቀብለው አነጋግረዋል። የሰሞኑ የአፍሪቃ ቀንድ መሪዎች አጋራ ጉብኝት እና ውይይት ጠ/ሚ ዐቢይ ወደ ስልጣን ከመጡ ወዲህ በጀመሩት አዲስ ግንኙነት ዕቅድ ላይ የተመሠረተ መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽሕፈት ቤት የፕረስ ሴክሬታሪያት ኃላፊ አቶ ንጉሡ ጥላሁን ለDW ገልጸዋል። ሱዳን ትሪቡን ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ ከጁባ ቀጥለው ወደ ኻርቱም ሱዳን ሊያደርጉት የነበረው ጉብኝት ድንገር መሰረዙን አመልክቷል፤ ይህንን ተያያዥ ጥያቄዎችን በማንሳት ዛሬ ከቀትር በኋላ በስልክ አቶ ንጉሡን አነጋግሬያለሁ።

ሸዋዬ ለገሠ

ተስፋለም ወልደየስ