1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአፍሪቃ ሕብረት የተኩስ አቁም ጥሪ

ሰኞ፣ ጥር 30 2014

ሕብረቱ ኢትዮጵያ ውስጥ ጦርነት ከተከሰተ ጊዜ ጀምሮ ለመፍትሔው ሲሠራ እንደቆየና የሰብዓዊ ድጋፍ በዓለም አቀፍ ሕግጋት እና መርሆዎች መሠረት ለሚገባው እንዲደርስ ብሎም የችግሩ መፍትሔም ፖለቲካዊ ነው ብሎ ሲንቀሳቀስ መቆየቱንም አስታውቋል።

https://p.dw.com/p/46deo
Äthiopien | AU Gipfel in Addis Abeba
ምስል Shadi Hatem/APA Images/ZUMAPRESS/picture alliance

«ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ፊትለፊት ንግግር እንዲካሄድ ጠይቋል»

የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት እንዲቆም ሁሉን አካታች እና ቅድመ ሁኔታ የሌለው የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረግ ሲወተውት መክረሙን የአፍሪካ ሕብረት አመለከተ። ሕብረቱ ኢትዮጵያ ውስጥ ጦርነት ከተከሰተ ጊዜ ጀምሮ ለመፍትሔው ሲሠራ እንደቆየና የሰብዓዊ ድጋፍ በዓለም አቀፍ ሕግጋት እና መርሆዎች መሠረት ለሚገባው እንዲደርስ ብሎም የችግሩ መፍትሔም ፖለቲካዊ ነው ብሎ ሲንቀሳቀስ መቆየቱንም አስታውቋል። ኢ ሕገ መንግሥታዊ የመንግሥት ለውጦች፣ መፈንቅለ መንግሥታት እና ሽብርተኝነት የአህጉሩ ፈታኝ የሰላምና ፀጥታ ችግሮች ናቸውም ብሏል። ሕብረቱ የኢትዮጵያ መንግሥት በሕግ አሸባሪ ከተባለው ሕወሓት ጋር ውይይት ያድርግ ማለቱን አንድ የፖለቲካ ተንታኝ ሕብረቱ በኢትዮጵያ ላይ ከምዕራባውያን ያልተለየ አቋም የማራመዱ ማሳያ ነው ብለውታል።
ዶቼ ቬለ ያነጋገራቸው የፖለቲካ ተንታኙ የአፍሪካ ሕብረት በዘላቂነት የአህጉሩን ሰላም ለመመለስ  የመሪዎችን የሥልጣን ጊዜ ወጥ በሆነ ሁኔታና በሕግ እንዲገደብ፣ እንዲሁም በአህጉሩ የጎሳ ፌዴራላዊ የመንግሥት አወቃቀርን በቻርተሩ ሊያግድ ይገባል ብለዋል።

ሰሎሞን ሙጬ 

ሸዋዬ ለገሠ

አዜብ ታደሰ