1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የድጋፍ እና የተቃውሞ ሰልፍ በብራሰልስ

ዓርብ፣ ኅዳር 7 2011

ሰልፉ የተካሄደው የጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድን የለውጥ መንግሥት ለመደገፍ ግን ደግሞ የለውጡ እርምጃ በርካታ አካባቢዎች ያልደረሰ መሆኑን ለመግለጽ እና በተለይ በአፋር ክልል አሁንም «አምባገነኖች» ያሏቸው ሥልጣን ላይ በመሆናቸው ወጣቶች እንደሚታሰሩ እና እንደሚንገላቱ ለማሳወቅ መሆኑን የሰልፉ አዘጋጆችና ተሳታፊዎች ለDW አስታውቀዋል።

https://p.dw.com/p/38NiP
Belgien Europäische Kommission in Brüssel
ምስል picture-alliance/dpa/D. Kalker

ላለፉት 6 ወራት ኢትዮጵያውያን በብራሰልስ አደባባዮችና ጎዳናዎች ሰልፍ መውጣታቸው ቀርቶ ነበረ። ትናንት ግን በአውሮጳ ህብረት ኮሚሽን ፊት ለፊት በሚገኘው የሹማን አደባባይ ሰላማዊ ሰልፍ አካሂደዋል። ሰልፉን የጠራው እና ያስተባበረው የአፋር ሰብዓዊ መብት ድርጅት ነው። ሰልፉ የተካሄደበት ምክንያትም የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር የዶክተር ዐብይ አህመድን የለውጥ መንግሥት ለመደገፍ ግን ደግሞ የለውጡ እርምጃ በርካታ አካባቢዎች ያልደረሰ መሆኑን ለመግለጽ እና በተለይ በአፋር ክልል አሁንም «አምባገነኖች» ያሏቸው በሥልጣን ላይ በመሆናቸው ወጣቶች ለእስር እና እንግልት እንደተዳረጉ ለማሳወቅ እንደሆነ የሰልፉ አዘጋጆች እና ተሳታፊዎች ለDW አስታውቀዋል። ያነጋገራቸው ብራሰልሱ ወኪላችን ገበያው ንጉሴ ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል።


ገበያው ንጉሴ 


ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ