1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአፋር ነዋሪዎች "መንግስት ጥቃቶችን ያስቁምልን" ሲሉ ጠየቁ

ማክሰኞ፣ ጥቅምት 4 2012

በአፋር ክልል በተለያዩ ጊዜያቶች የሚፈጠሩ ጥቃቶችን “የፌደራል መንግስቱ ያስቁምልን” ሲሉ የአፋር ማህብረሰብ አባላት ጠየቁ። በአፋር እስከ ትላንት ምሽት ድረስ የቆየውን የመንገድ መዝጋት አድማ ያስተባበሩ እና የተሳተፉ የህብረተሰብ አባላት ለDW እንደተናገሩት “የፌደራል መንግስት ለጉዳዩ ትኩረት ሰጥቶ ዘላቂ መፍትሄ ማፈላለግ አለበት።”

https://p.dw.com/p/3RLlT
12.06.2013 DW Online Karten Basis Äthiopien Englisch

የአፋር ነዋሪዎች "መንግስት ጥቃቶችን ያስቁምልን" ሲሉ ጠየቁ

በአፋር ክልል በተለያዩ ጊዜያት የሚታዩትን ጥቃቶች የፌደራል መንግሥት ያስቁምልን ሲሉ የአፋር ማኅበረሰብ አባላት ጠየቁ። ወኪላችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ባደረሰን መረጃ መሰረት ባለፉት ሁለት ቀናት በአፋር ክልል የመንገድ መዝጋት አድማ ያስተባበሩና የተሳተፉ አባላት ለዶይቼ ቬለ እንደተናገሩት ፌደራል መንግሥት ለጉዳዩ ትኩረት ሰጥቶ መፍትሄ ማፈላለግ አለበት ሲሉ ገልፀዋል።

አፋሮች የታጠቁ እና የተደራጁ ባልዋቸዉ የኢሳ ጎሳ አባላት ደረሰብን ባሉት ጥቃት እና የክልሉ ልዩ ኃይል ከገዳማይቱ አዳይቱ እና እንድፋኦ እንዲወጣ መደረጉን ተከትሎ ዋናዉ የአዲስ አበባ አዋሽ ድሬዳዋ እንዲሁም ሌሎች መጋቢ መስመሮችን የመዝጋት አድማ ማድረጋቸዉ ተገልፆአል።  ተዘግተዉ የነበሩት የአዲስ አበባ አዋሽ ድሬደዋ እንዲሁም ሌሎች መጋቢ መስመሮች ሁሉ  ከትናንት ምሽት 11 ሰዓት ጀምሮ ለተሽከርካሪ ክፍት መሆናቸዉን ወደ አዋሽ ከተማ የተጓዘው የዶይቼ ቬለ ዘጋቢ ተመልክቷል። 

ዝርዝር ዘገባውን ለማድመጥ የድምጽ ማዕቀፉን ይጫኑ። 

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር 

ተስፋለም ወልደየስ
ሸዋዬ ለገሠ