የአፋር ባሕላዊ ሕግ
ሐሙስ፣ ነሐሴ 17 2010ማስታወቂያ
የአፋር ሕዝብ የሚዳኝባቸዉ ባሕላዊ ሕግጋት አሉት።ጥፋተኛ ወይም ተጠርጣሪ የሚዳኝባቸዉ የሕግ ሒደቶች፤ ደንቦች፤ ፍርዶች እና ተበዳይ የሚካስባቸዉ ሕጎች እና ሽምግልናዎች በአብዛኛዉ የአፋር ሕዝብ ዘንድ አሁንም ድረስ ተቀባይነት አላቸዉ።በሕጉ መሠረት ጥፋተኛዉ ላይ የሚጣለዉ ቅጣት በግመል የሚሠላ ነዉ።የአካባቢዉ ሕዝብ ወይም ጥፋተኛዉ ቅጣቱን በግመል መክፈል ካልቻለ ግን ቅጣቱ እንደ የአካባቢዉ ወደ ሌሎች እንስሳቶች ይመነዘራል።በዛሬዉ የባሕል መድረግ ዝግጅታችን የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ሥለ አፋር ሕዝብ ባሕላዊ ሕጎች ያወጋናል።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ