1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአዳማ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ከዩኒቨርስቲ ግቢ መታገዳቸዉ

ማክሰኞ፣ ጥር 14 2011

የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የቅድመ ምረቃ መደበኛ ተማሪዎች ከዚህ በፊት ቃል የተገባልን ይፈጸምልን በሚል ያነሱት ጥያቄ ያስከተለው ውዝግብ ምላሽ ባለማግኘቱ ከ1ኛ እስከ 5ኛ ዓመት ያሉ 5400 ተማሪዎች የግማሽ ዓመቱን ትምህርት በአግባቡ አልተማራችሁም ለምዘናም ብቁ አይደላችሁም በሚል ከግቢው እንዲወጡ ተደረገ።

https://p.dw.com/p/3ByVT
Äthiopien, Adama
ምስል DW/M. Yonas Bula

አግባቡ አልተማራችሁም ለምዘናም ብቁ አይደላችሁም በሚል ከግቢው እንዲወጡ ተደረገ

የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የቅድመ ምረቃ መደበኛ ተማሪዎች ከዚህ በፊት ቃል የተገባልን ይፈጸምልን በሚል ያነሱት ጥያቄ ያስከተለው ውዝግብ ምላሽ ባለማግኘቱ ከ1ኛ እስከ 5ኛ ዓመት ያሉ 5400 ተማሪዎች የግማሽ ዓመቱን ትምህርት በአግባቡ አልተማራችሁም ለምዘናም ብቁ አይደላችሁም በሚል ከግቢው እንዲወጡ ተደረገ። ተማሪዎቹ ከዚህ በፊት ተቋሙን ይመሩ የነበሩ ኃላፊዎች በተለይም እንደተመረቃችሁ ሥራ ትይዛላችሁ፡ የቀጣይ እርከን ነጻ የትምህርት እድል ይሰጣችኋል፡ እና መሰል ቃል የተገቡልን ጉዳዮች  ምላሽ አጣን ቢሉም፤ አሁን ተቋሙን የሚመሩት ሰዎች ደግሞ ተገባ የተባለው ቃል በማስረጃ እና በሰነድ ያልተደገፈ ከመሆኑም ባሻገር ዩኒቨርሲቲው ሊያደርገው የማይችልው በመሆኑ ተቀባይነት የሌለው ጥያቄ ነው በሚል ክርክር መማር ማስተማሩ ሲስተጓጎል ቆይቶ እልባት ባለማግኘቱ ተማሪዎቹ ግቢው እንዲወጡ እና የካቲት 25 እና 26 እንደገና ዳግም የመጀመርያው ወሰነ ትምህርት ምዝገባ ተደርጎ ትምህርት እንዲጀመር ሲል ወስኗል። ጉዳዩ በብዙ መስፈር ጎድቶናል የሚሉት ተማሪዎቹ የአንድ ወሰነ ትምህርት ጊዜ ከመባከኑም በላይ የመማር ፍላጎታችን ላይም አሉታዊ ተጽእኖ አሳርፎብናል ብለዋል። የዩኒቨርሲቲው ሴኔት እነዚህ 5400 ተማሪዎች ከነገ የካቲት 15 ጀምሮ የተቋሙን ምንም አይነት አገልግሎት ማግኘት እንደማይችሉ በማስታወቂያ ማሳወቁን ተከትሎ ተማሪዎቹ ሻንጣቸውን ይዘው ግቢውን እየለቀቁ ነው። አሁን በዩኒቨርሲቲው እየተማሩ የሚገኙትም የማስተርስ፡ የዶክትሬት፡ የተከታታይ የርቀትና የማታ ተማሪዎች ብቻ መሆናቸውን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶክተር ለሚ ጉታ አስታውቀዋል።


ሰለሞን ሙጬ
አዜብ ታደሰ 
እሸቴ በቀለ